የ ጽሁፍ ሰነዶችን በ HTML አቀራረብ ማስቀመጫ

እርስዎ ማስቀመጥ ይችላሉ የ LibreOffice ጽሁፍ ሰነድ በ HTML አቀራረብ: እና በ ዌብ መቃኛ ሊያዩት ይችላሉ: እርስዎ ከፈለጉ: ማዛመድ ይችላሉ የ ገጽ መጨረሻ ከ ተወሰነ የ ራስጌ አንቀጽ ዘዴ ጋር እንዲያመነጭ የ ተለየ የ HTML ገጽ ዘዴው በሚታይ ጊዜ በ ሰነድ ውስጥ: LibreOffice የ ጽሁፍ ሰነድ ራሱ በራሱ ገጽ ይፈጥራል የ hyperlinks ለ እያንዳንዱ እነዚህ ገጾች

እርስዎ የ ጽሁፍ ሰነድ በ HTML አቀራረብ ሲያስቀምጡ: ማንኛውም ንድፍ በ ሰነዱ ውስጥ የሚቀመጠው በ HTML ሰነድ ዳታ ማስተላለፊያ ማጣበቂያ ነው: LibreOffice የ ዋናውን ንድፍ አቀራረብ ለ ማስቀመጥ ይሞክራል: እንደ: JPEG ስእሎች ወይንም SVG ምስሎች ይቀመጣሉ በ HTML አቀራረብ: ሁሉም ሌሎች የ ንድፍ አቀራረብ የሚቀመጡት እንደ PNG. ነው

  1. አንዱን ነባር ይፈጽሙ LibreOffice የ ራስጌ አንቀጽ ዘዴ: ለምሳሌ:"ራስጌ 1": ለ አንቀጽ አዲስ የ HTML ገጽ ማመንጨት በሚፈልጉበት

  2. ይምረጡ ፋይል - መላኪያ - የ HTML ሰነድ መፍጠሪያ

  3. ዘዴዎች ሳጥን ውስጥ ይምረጡ መጠቀም የሚፈልጉትን የ አንቀጽ ዘዴ አዲስ የ HTML ገጽ እንዲያመነጭ

  4. መንገድ እና ስም ያስገቡ ለ HTML ሰነድ እና ከዛ ይጫኑ ማስቀመጫ.

Please support us!