LibreOffice 25.2 እርዳታ
ክፍሎች የተሰየሙ የ ጽሁፍ አካሎች ናቸው: ንድፎችን እና እቃዎችን ያካትታሉ እርስዎ በተለያየ መንገድ የሚጠቀሙበት
ጽሁፍ እንዳይታረም ለመጠበቅ
ጽሁፍ ለማሳያ ወይንም ለመደበቂያ
ጽሁፍ እና ንድፎች እንደገና ለ መጠቀም ከ ሌላ LibreOffice ሰነዶች ውስጥ
ከ አሁኑ የ ገጽ ዘዴ የ ተለየ የ አምድ እቅድ የሚጠቀም የ ጽሁፍ ክፍሎች ለማስገባት
ክፍል ቢያንስ አንድ አንቀጽ ይይዛል: እርስዎ ጽሁፍ በሚመርጡበት እና ክፍል በሚፈጥሩበት ጊዜ: የ አንቀጽ መጨረሻ ራሱ በራሱ ይገባል ከ ጽሁፉ መጨረሻ በኩል
እርስዎ ከ ጽሁፍ ሰነድ ውስጥ ክፍሎች ማስገባት ይችላሉ: ወይንም ጠቅላላ ሰነድ እንደ ክፈል ወደ ሌላ የ ጽሁፍ ሰነድ ማስገባት ይችላሉ: እንዲሁም እርስዎ ክፍሎች ወደ ጽሁፍ ሰነድ እንደ አገናኝ ወደ ሌላ ሰነድ ማስገባት ይችላሉ: ወይንም ወደ ተመሳሳይ ሰነድ
አዲስ አንቀጽ ለማስገባት ወዲያውኑ ከ ክፍል በፊት ወይንም በኋላ: ይምረጡ ከ ክፍል በፊት ወይንም በኋላ እና ከዛ ይጫኑ ምርጫ Alt+ማስገቢያ
እርስዎ በ ነበረው ክፍል ውስጥ ክፍሎች መጨመር ይችላሉ: ለምሳሌ: እርስዎ ማስገባት ይችላሉ ሁለት አምዶች ያለው ክፍል ወደ አንድ አምድ ያለው ክፍል ውስጥ
የ ክፍል እቅድ: ለምሳሌ: በ አምዶች ቁጥር ላይ: ቅድሚያ ይኖረዋል ከ ተገለጸው ገጽ እቅድ በፊት በ ገጽ ዘዴ ውስጥ