የ መግለጫ አጠቃቀም

በ ጽሁፍ ሰነድ ውስጥ: እርስዎ መጨመር ይችላሉ ተከታታይ የ ቁጥር መግለጫ ለ ንድፎች: ሰንጠረዦች: ክፈፎች: እና መሳያ እቃዎች

እርስዎ ማረም ይችላሉ የ ጽሁፍ እና የ ቁጥር መጠኖችን ለተለያዩ አይነት መግለጫዎች

የ ማስታወሻ ምልክት

እርስዎ ለ ስእል ወይንም እቃ መግለጫ ጽሁፉ ሲያስገቡ: እቃው እና መግለጫ ጽሁፉ በ አዲስ ክፈፍ ውስጥ ይቀመጣሉ: መግለጫ ለ ሰንጠረዥ ሲያስገቡ: የ መግለጫ ጽሁፉ ይገባል እንደ አንቀጽ ከ ሰንጠረዡ አጠገብ: መግለጫ ለ ክፈፍ ሲያስገቡ: የ መግለጫ ጽሁፉ ይጨመራል ወደ ጽሁፉ በ ክፈፍ ውስጥ: ከ ነበረው ጽሁፍ በፊት ወይንም በኋላ:


የ ምክር ምልክት

ለማንቀሳቀስ ሁለቱንም እቃውን እና መግለጫውን: ይጎትቱ ክፈፉን እነዚህን እቃዎች የያዘውን: የ መግለጫውን ቁጥር ለማሻሻል ክፈፉን ካንቀሳቀሱ በኋላ ይጫኑ F9.


መግለጫ ለ መግለጽ እንደሚከተለው ያድርጉ:

  1. ይምረጡ እቃውን መግለጫ መጨመር የሚፈልጉትን

  2. ይምረጡ ማስገቢያ - መግለጫ

  3. ይምረጡ የሚፈልጉት ምርጫ እና ከዛ ይጫኑ እሺ እርስዎ ከፈለጉ የተለየ ጽሁፍ ማስገባት ይችላሉ በ ምድብ ሳጥን ውስጥ ለምሳሌ ቅርጽ

የ ማስታወሻ ምልክት

የ መግለጫ ጽሁፉን በቀጥታ ከ ሰነዱ ላይ ማረም ይችላሉ


የ መግለጫ ጽሁፍ የሚቀርበው በ አንቀጽ ዘዴ ነው ተመሳሳይ ስም ባለው የ መግለጫ ምድብ: ለምሳሌ: እርስዎ ካስገቡ የ "ሰንጠረዥ" መግለጫ: የ "ሰንጠረዥ" አንቀጽ ዘዴ የ መግለጫ ጽሁፍ ይፈጸማል

የ ምክር ምልክት

LibreOffice እቃ ሲጨምሩ ራሱ በራሱ መግለጫ ይጨምራል: ንድፎች: ክፈፎች ወይንም ሰንጠረዥ ይምረጡ - LibreOffice መጻፊያ - በራሱ መግለጫ


Please support us!