የ ሰንጠረዥ ስሌቶችን ውጤት በ ሌላ ሰንጠረዥ ውስጥ ማሳያ

የ ሰንጠረዥ ስሌቶችን በ አንድ ክፍል ማስሊያ እና ውጤት በ ሌላ ሰንጠረዥ ውስጥ ማሳያ

  1. የ ጽሁፍ ሰንጠረዥ ይክፈቱ: በርካታ አምዶች እና ረድፎች ያሉት ሰንጠርዥ ያስገቡ: እና ከዛ አንድ ክፍል ያለው ሌላ ሰንጠረዥ ያስገቡ

  2. ቁጥር ያስገቡ ወደ አንዱ ትልቅ ክፍል ሰንጠረዥ ውስጥ

  3. መጠቆሚያውን ነጠላ በሆነ ሰንጠረዥ ውስጥ ያድርጉ እና ከዛ ይጫኑ F2

  4. መቀመሪያ መደርደሪያ ውስጥ መፈጸም የሚፈልጉትን ተግባር ያስገቡ ለምሳሌ =ድምር

  5. ይጫኑ በ ክፍል ውስጥ በ ትልቅ ሰንጠረዥ ቁጥር የያዘውን እና ይጫኑ የ መደመሪያ ምልክት (+) እና ከዛ ይጫኑ የተለየ ክፍል ቁጥር የያዘውን

  6. ይጫኑ ማስገቢያ

የ ማስታወሻ ምልክት

እርስዎ ከፈለጉ የ ሰንጠረዥ አቀራረብን እንደ መደበኛ ጽሁፍ እንዲሆን ማድረግ ይችላሉ: ሰንጠረዡን ወደ ክፈፍ ያስገቡ: እና ከዛ ክፈፉን እንደ ባህሪ ያስቁሙ: ክፈፉ ይቆማል ጽሁፍ ለማስተካከል ጽሁፍ ሲያስገቡ ወይንም ሲያጠፉ


Please support us!