በተጠቃሚው የሚወሰኑ ድንበሮች በ ጽሁፍ ሰነዶች ውስጥ

እርስዎ መፈጸም ይችላሉ የ ተለያዩ የ ክፍል ድንበሮች ለ ተመረጡት ክፍሎች: በ መጻፊያ ሰንጠረዥ ውስጥ እና ለ ጠቅላላው ሰንጠረዥ: ሌሎች እቃዎች በ ጽሁፍ ሰነዶች ውስጥ በ ተጠቃሚ የ ተወሰነ ዽንበሮች ሊኖራቸው ይችላል: ፤እምሳሌ: እርስዎ መመደብ ይችላሉ ለ ድንበሮች የ ገጽ ዘዴዎች: ለ ክፈፎች: እና ለ ገቡ ስእሎች ወይንም ቻርትስ

  1. ይምረጡ ክፍል ወይንም በርካታ ክፍሎች በ መጻፊያ ሰንጠረዥ ውስጥ

  2. ይምረጡ ሰንጠረዥ - ባህሪዎች

  3. ከ ንግግሩ ውስጥ ይጫኑ ድንበሮች tab.

  4. ይምረጡ የ ድንበር ምርጫዎች መፈጸም የሚፈልጉትን እና ይጫኑ እሺ

ከ ምርጫዎች በ መስመር ማዘጋጃ ቦታ ለ በርካታ ድንበር ዘዴዎች መፈጸሚያ መጠቀም ይችላሉ

ክፍሎችን መምረጫ

እንደ ክፍሉ ምርጫ ቦታው የተለያየ መልክ ይኖረዋል

ምርጫዎች

የ መስመር ቦታ አዘገጃጀት

አንድ ክፍል ተመርጧል ከ ሰንጠረዥ ውስጥ ከ አንድ በላይ ክፍሎች ያሉት: ወይንም መጠቆሚያው ምንም ክፍል ባልተመረጠበት ሰንጠረዥ ውስጥ ነው

የ አንድ ክፍል ድንበር

ባለ አንድ ክፍል ሰንጠረዥ: ይህ ክፍል ተመርጧል

አንድ የ ተመረጠ የ ክፍል ድንበር

ከ አምዱ ውስጥ ክፍሎች ተመርጠዋል

የ ተመረጠው የ አምድ ድንበር

ከ ረድፉ ውስጥ ክፍሎች ተመርጠዋል

ለ ረድፍ የ ተመረጠው ድንበር

ጠቅላላ ሰንጠረዡ የ 2x2 ወይንም ተጨማሪ ክፍሎች ተመርጠዋል

የ ተመረጠውን ድንበር መከልከያ


ነባር ማስናጃዎች

ይጫኑ አንዱን ከ ነባር ምልክቶች በርካታ ድንበሮችን ለማሰናጃ ወይንም እንደነበር ለመመለሻ

ለምሳሌ

Select a block of about 8x8 cells, then choose Table - Properties - Borders tab.

ለ ድንበር ነባር ምልክት

የሚቀጥለው መስመር በ የትኛው ምልክት እንደሚሰናዳ ወይንም እንደሚወገድ አሁን ለ እርስዎ ይታያል

በ ተጠቃሚ የሚወሰኑ ማሰናጃዎች

ተጠቃሚው የሚወሰን ቦታ፡ ይጫኑ ለ ማዘጋጀት ወይንም ለማስወገድ እያንዳንዱን መስመር፡ ቅድመ እይታው የሚያሳያቸው መስመሮች በ ሶስት የተለያያ ሁኔታ ነው

በተከታታይ ይጫኑ በ ጠርዙ ወይንም በ ድንበሩ ላይ ለ መቀያየር ሶስቱን የተለያዩ ሁኔታዎች

የ መስመር አይነቶች

ምስል

ትርጉም

ጥቁር መስመር

ሙሉ መስመር ለ ድንበር

የ ጥቁር መስመር ማሰናጃ ለ ተመሳሳይ መስመር ለ ተመረጡት ክፍሎች: መስመሩ የሚታየው በ ነጠብጣብ መስመር ነው እርስዎ ሲመርጡ የ 0.05 ነጥብ መስመር ዘዴ: ድርብ መስመሮች የሚታዩት እርስዎ የ ድርብ መስመር ዘዴ ሲመርጡ ነው

ግራጫ መስመር

ግራጫ መስመር ለ ድንበር

ግራጫ መስመር ይታያል: ተመሳሳይ መስመር ለ ክፍሉ ሲመረጥ አይቀየርም: በዚህ ቦታ ላይ ምንም መስመር አይሰናዳም ወይንም አይወገድም

ነጭ መስመር

ነጭ መስመር ለ ድንበር

ነጭ መስመር ይታያል: ተመሳሳይ መስመር ለ ክፍሉ ሲመረጥ ይወገዳል


ለምሳሌ

  1. ይምረጡ ነጠላ ክፍል ከ መጻፊያ ሰንጠረዥ ውስጥ: እና ከዛ ይምረጡ ሰንጠረዥ - ባህሪዎች - ድንበሮች

  2. ወፍራም የ መስመር ዘዴ ይምረጡ

  3. የ ታችኛውን ድንበር ለማሰናዳት ይጫኑ የ ታችኛውን ጠርዝ በተከታታይ መስመሩ ወፍራም እስኪሆን ድረስ

sወፍራም ድንበር ከ ታች ማሰናጃ

note

በ መጻፊያ ሰንጠረዥ ውስጥ ሁሉም ክፍሎች ቢያንስ የ ግራ እና የ ታች መስመር ይኖራቸዋል በ ነባር: አብዛኞቹ ክፍሎች በ ሰንጠረዥ ላይ የሚቀጥል ተጨማሪ መስመር መፈጸም ይችላሉ በ ነባር


warning

ሁሉም መስመሮች በ ቅድመ እይታ ጊዜ በ ነጭ የታዩት ከ ክፍሉ ውስጥ ይወገዳሉ


ለ ባህሪዎች: ድንበር መግለጫ

ለ ገጾች ድንበሮች መግለጫ

ድንበሮች እና አንቀጾች መግለጫ

Please support us!