ራሱ በራሱ ፊደል ማረሚያ

ማድረግ ይችላሉ LibreOffice ራሱ በራሱ ፊደል እንዲያርም እርስዎ በሚጽፉበት ጊዜ የተሳሳተ የፊደል ግድፈት ሲያገኝ በ ቀይ ማዕበል መስመር ከ ስሩ እንዲያሰምርበት

በሚጽፉ ጊዜ ራሱ በራሱ ፊደል ማረሚያ ማስቻያ

  1. ይምረጡ መሳሪያዎች - ራሱ በራሱ ፊደል ማረሚያ

  2. በ ቀኝ-ይጫኑ ቃላት ከስሩ በ ቀይ ማእበል የተስመረበትን እና ከዛ ይምረጡ የሚመከሩትን መቀየሪያ ቃላት ከ ዝርዝር ውስጥ ወይንም ከ በራሱ አራሚ ንዑስ ዝርዝር ውስጥ

ቃላት ከመረጡ ከ በራሱ አራሚ ንዑስ ዝርዝር ውስጥ ከስሩ የተሰመረበት እና የተቀየረውን ቃላት ራሱ በራሱ ወደ በራሱ አራሚ ዝርዝር ውስጥ ይጨምረዋል ለ አሁኑ ቋንቋ: የ በራሱ አራሚ ዝርዝርን ለ መመልከት ይምረጡ መሳሪያዎች – በራሱ አራሚ ምርጫዎች እና ከዛ ይጫኑ የ መቀየሪያ tab.

እንዲሁም ከስሩ የተሰመረበትን ቃል ወደ ማስተካከያ መዝገበ ቃላት መጨመር ይችላሉ ይምረጡ መጨመሪያ.

ቃሎችን ከ ፊደል ማረሚያው ለማስቀረት

  1. ማስቀረት የሚፈልጉትን ቃሎች ይምረጡ

  2. ይጫኑ የ ቋንቋ መቆጣጠሪያ በ ሁኔታዎች መደርደሪያ ላይ ዝርዝር ለመክፈት

  3. ይምረጡ “ምንም (ፊደሉን አታርም)”

አዲስ መዝገበ ቃላት መፍጠሪያ

ወደ በራሱ አራሚ የተለዩ ዝርዝር መጨመሪያ

ፊደል እና ሰዋሰው በማረም ላይ

Please support us!