በሚጽፉ ጊዜ ቁጥር ወይንም ነጥብ የተሰጠው ዝርዝር መፍጠሪያ

LibreOffice በሚጽፉ ጊዜ ራሱ በራሱ ቁጥር ወይንም ነጥብ መስጫ መፈጸሚያ

ራሱ በራሱ ቁጥር እና ነጥብ መስጫ ማስቻያ

  1. ይምረጡ መሳሪያዎች - በራሱ አራሚ - በራሱ አራሚ ምርጫዎች ይጫኑ የ ምርጫዎች tab: እና ከዛ ይምረጡ “ቁጥር መስጫ መፈጸሚያ – ምልክት”

  2. ይምረጡ መሳሪያዎች - በራሱ አራሚ እና ያረጋግጡ በምጽፍበት ጊዜ መመረጡን

የ ምክር ምልክት

ራሱ በራሱ ቁጥር መስጫ ምርጫ የሚፈጸመው በ አንቀጾች አቀራረብ ሲጠቀሙ ነው በ "ነባር": "የ ጽሁፍ ሰውነት": ወይንም "የ ጽሁፍ ሰውነት ማስረጊያ" በ አንቀጽ ዘዴ ውስጥ


በሚጽፉ ጊዜ ቁጥር ወይንም ነጥብ የተሰጠው ዝርዝር መፍጠሪያ

  1. ይጻፉ 1., i., ወይንም I. ቁጥር መስጫ ዝርዝር ለማስጀመር ይጻፉ * ወይንም - ነጥብ መስጫ ዝርዝር ለማስጀመር: እንዲሁም የ ቀኝ ቅንፍን መጻፍ ይችላሉ ከ ቁጥሩ በኋላ በ ነጥብ ፋንታ ለምሳሌ 1) ወይንም i).

  2. ክፍተት ያስገቡ ጽሁፍ ይጻፉ እና ካዛ ማስገቢያውን ይጫኑ: አዲሱ አንቀጽ ራሱ በራሱ የሚቀጥለውን ቁጥር ወይንም ነጥብ ያገኛል

  3. ዝርዝሩን ለመጨረስ ማስገቢያውን እንደገና ይጫኑ

የ ማስታወሻ ምልክት

የ ቁጥር መስጫ ዝርዝር ከ ማንኛውም ቁጥር ማስጀመር ይችላሉ


Changing the List Level of a List Paragraph

Please support us!