ሜዳዎች

ወደ እርስዎ ተንሸራታች ሊያስገቡ የማይችሉት የ መደበኛ ሜዳዎች ዝርዝር

በ ተንሸራታቹ ውስጥ ሜዳ ማረም ከፈለጉ ይምረጡት እና ይምረጡ ማረሚያ – ሜዳዎች

ይህን ትእዛዝ ለ መፈጸም...

ይምረጡ ማስገቢያ - ሜዳ


ቀን (የተወሰነ)

የ አሁኑን ቀን ማስገቢያ ወደ እርስዎ ተንሸራታች እንደ ተወሰነ ሜዳ፡ ቀኑ ራሱ በራሱ አይሻሻልም

ቀን (ተለዋዋጭ)

የ አሁኑን ቀን ማስገቢያ ወደ እርስዎ ተንሸራታች እንደ ተለዋዋጭ ሜዳ፡ ቀኑ ራሱ በራሱ ይሻሻላል ፋይሉን በሚጭኑ ጊዜ

ሰአት (የተወሰነ)

የ አሁኑን ሰአት ወደ ተንሸራታች ማስገቢያ እንደ ተወሰነ ሰአት ሜዳ: ሰአቱ ራሱ በራሱ አይሻሻልም

ሰአት (ተለዋዋጭ)

የ አሁኑን ሰአት ወደ ተንሸራታች ማስገቢያ እንደ ተለዋዋጭ ሜዳ: ሰአቱ ራሱ በራሱ ይሻሻላል ፋይሉን እንደገና በሚጭኑ ጊዜ

ደራሲው

የ መጀመሪያ ስም እና የ አባት ስም ማስገቢያ ከዝርዝር ውስጥ ከ LibreOffice ተጠቃሚ ዳታ ወደ ንቁ ተንሸራታች

የ ገጽ ቁጥር

ወደ አሁኑ ተንሸራታች ወይንም ገጽ ውስጥ የ ገጽ ቁጥር መጨመሪያ እርስዎ ለ እያንዳንዱ ተንሸራታች የ ገጽ ቁጥር መጨመር ከ ፈለጉ: ይምረጡ መመልከቻ - ዋናው እና የ ገጽ ቁጥር መጨመሪያ ሜዳ ያስገቡ: የ ቁጥር አቀራረብ ለ መቀየር: ይምረጡ - ባህሪዎች - ገጽ tab እና ከዛ ይምረጡ አቀራረብ ከ ዝርዝር ውስጥ ከ እቅድ ማሰናጃ ቦታ ውስጥ:

የ ፋይል ስም

ንቁ የሆነውን ፋይል ስም ማስገቢያ፡ ስሙ የሚታየው ፋይሉን ካስቀመጡ በኋላ ነው

Please support us!