LibreOffice 24.8 እርዳታ
በ ሰነድ ውስጥ የ አቀራረብ ለውጦችን መግለጫ
በ እርስዎ የ ጽሁፍ ወይንም ሰንጠረዥ ሰነድ ውስጥ ለውጦችን ለ መመዝገብ ወይንም ለማሳየት: ይምረጡ ማረሚያ - ለውጦችን መከታተያ - መመዝገቢያ ወይንም ማረሚያ - ለውጦችን መከታተያ - ማሳያ
የ ተመዘገቡ ለውጦችን ማሳያ ማሰናጃ መግለጫ: ይምረጡ የ ለውጥ አይነቶች እና ተመሳሳይ ማሳያ ባህሪዎች እና ቀለም: በ ቅድመ እይታ ሜዳዎች ለ ማሳየት ውጤቱን የ ተመረጠውን ምርጫ ማሳያ
ጽሁፍ በ ሰነዱ ውስጥ በሚገባ ጊዜ ለውጡ እንዴት እንደሚታይ መወሰኛ
ጽሁፍ በ ሰነዱ ውስጥ በሚጠፋ ጊዜ ለውጡ እንዴት እንደሚታይ መወሰኛ: እርስዎ ጽሁፍ ሲጠፋ የሚመዘግቡ ከሆነ: ጽሁፉ ይታያል ከ ተመረጠው ባህሪ ጋር (ለምሳሌ: በላዩ ላይ መሰረዣ) እና በማይጠፋ ጊዜ
ለ ጽሁፍ ባህሪዎች ለውጦች እንዴት እንደሚታዩ መወሰኛ: እነዚህ ለውጦች በ ባህሪ ላይ ተጽእኖ ይፈጥራሉ እንደ ማድመቂያ: ማዝመሚያ ወይንም ከ ስሩ ማስመሪያ አይነት
እርስዎ እንዲሁም ቀለም መምረጥ ይችላሉ ለ ማሳየት እያንዳንዱን አይነት የሚመዘገበውን ለውጥ: እርስዎ ሁኔታውን በሚመርጡ ጊዜ "በ ደራሲ" በ ዝርዝር ውስጥ ቀለም ራሱ በራሱ ይወስናል ለ LibreOffice, እና ከዛ ያሻሽላል እንዲመሳሰል ከ ደራሲው እያንዳንዱ ለውጦች ጋር
የ የትኛው መስመር ጽሁፍ እንደ ተቀየረ ለማሳየት: እርስዎ መግለጽ ይችላሉ ምልክት እንዲታይ በ ግራ ወይንም በ ቀኝ የ ገጽ ጠርዝ በኩል
በ ሰነዱ ውስጥ የ ተቀየረው መስመር የት እንደሆነ መግለጫ እርስዎ ምልክት ማድረጊያ ማሰናዳት ይችላሉ ስለዚህ ሁል ጊዜ ይታያል በ ግራ ወይንም በ ቀኝ መስመር በኩል ወይንም በ ውጪ ወይንም በ ውስጥ መስመር በኩል
በ ጽሁፍ ሰነድ ውስጥ ለ ተቀየሩ መስመሮች ማድመቂያ ቀለም መወሰኛ