LibreOffice 24.8 እርዳታ
የ መገምገሚያ ተግባር ዝግጁ ነው ለ LibreOffice ጽሁፍ ሰነዶች እና ሰንጠረዥ ሰነዶች
ለ መጠበቅ የ ተፈጸሙ ለውጦችን በ ሰነድ ውስጥ በሚታረም ጊዜ: ይምረጡ ማረሚያ - ለውጦች መከታተያ - ለውጦች መጠበቂያ ተግባሩን ለማጥፋት ወይንም ለ መቀበል ወይንም ላለ መቀበል ለውጦችን: በ መጀመሪያ ትክክለኛውን የ መግቢያ ቃል ማስገባት በጣም አስፈላጊ ነው:
ይምረጡ መጠበቂያ ይህ ይከፍታል የ መግቢያ ቃል ንግግር
የ መግቢያ ቃል ያስገቡ ቢያንስ አንድ ባህሪ የያዘ እና ያረጋግጡ: ይጫኑ እሺ