እትሞች ማዋሀጃ

note

የ መገምገሚያ ተግባር ዝግጁ ነው ለ LibreOffice ጽሁፍ ሰነዶች እና ሰንጠረዥ ሰነዶች


ሰነድ በሚታርረም ጊዜ ከ አንድ በ ላይ በሆኑ ሰዎች: የ ታረሙትን ኮፒዎች ማዋሀድ ይቻላል ወደ ዋናው ሰነድ ውስጥ: የሚያስፈልገውም ሰነዶቹ መለያየታቸውን ብቻ ነው: በ ተመዘገበው ለውጦች ላይ - ሁሉም ሌሎች ዋናው ጽሁፍ ተመሳሳይ መሆን አለበት

  1. እርስዎ ሁሉንም ኮፒዎች ማዋሀድ የሚፈልጉበትን ዋናውን ሰነድ መክፈቻ

  2. ይምረጡ ማረሚያ - ለውጦች መከታተያ - ሰነድ ማዋሀጃ የ ፋይል ምርጫ ንግግር ይታያል

  3. ይምረጡ የ ሰነድ ኮፒ ከ ንግግር ውስጥ: በ ዋናው ሰነድ ላይ ምንም ለውጥ ከሌለ: ኮፒው ከ ዋናው ሰነድ ጋር ይዋሀዳል

    በ ዋናው ሰነድ ውስጥ ለውጥ ከ ተፈጸመ: የ ስህተት ንግግር ይታያል ለ እርስዎ ውህደቱ እንዳልተሳካ የሚገልጽ

  4. እርስዎ ሰነዶች ካዋሀዱ በኋላ ለ እርስዎ ይታያል የ ተቀረጸው ለውጦች ከ ዋናው ሰነድ ውስጥ ኮፒ የተደረገው

Please support us!