LibreOffice 24.8 እርዳታ
ይምረጡ ፋይል - አዲስ - የ ንግድ ካርድ ለ መክፈት የ ንግድ ካርድ ንግግር: የ እርስዎ የ ንግድ ካርድ ምን እንደሚመስል ማየት ያስችሎታል
እርስዎ ሁለቱንም መንደፍ ይቻላሉ የ ንግድ ካርድ እና ምልክቶች በ ንግግር ውስጥ
ይምረጡ ፋይል - አዲስ - ምልክቶች ለ መክፈት የ ምልክቶች ንግግር
በ ምልክቶች tab: ውስጥ አቀራረብ የሚገልጸው የ ምልክት አቀራረብ ነው
LibreOffice መጻፊያ በርካታ ዝግጁ የ ወረቀት አቀራረብ ለ ምልክቶች: አርማዎች: እና ለ ንግድ ካርዶች ይዟል: እርስዎ እንዲሁም ሌሎች መጨመር ይችላሉ በ ተጠቃሚ-የሚገለጽ አቀራረብ
በ ምልክቶች tab: ውስጥ መቅረጫ እርስዎ ይምረጡ በ ምልክት ላይ የሚጻፈውን
ይህ ብዙ ጊዜ የ ዳታቤዝ ሜዳዎች ያካትታል: ስለዚህ ምልክቶቹን ማተም ይቻላል ከ ተቀየሩ ይዞታዎች ጋር: በሚልኩ ጊዜ የ "ፎርም ደብዳቤዎች" ለምሳሌ: ተመሳሳይ ጽሁፍ ማተም ይቻላል በ ሁሉም ምልክቶች ላይ
ይጠቀሙ የ ዳታቤዝ እና ሰንጠረዥ ዝርዝር ሳጥኖች ለ መምረጥ የ ዳታቤዝ እና ሰንጠረዥ ከ ዳታ ሜዳዎች ከሚገኙበት: ይጫኑ በ ቀስት ቁልፍ ላይ የ ተመረጠውን ዳታ ሜዳ ለማስተላለፍ ወደ መቅረጫ ቦታ: ይጫኑ ማስገቢያውን የ መስመር መጨረሻ ለማስገባት: እርስዎ እንዲሁም ክፍተት እና ሌሎች የ ተወሰኑ ጽሁፎች ማስገባት ይችላሉ
በ አቀራረብ tab እርስዎ መግለጽ ይችላሉ የራስዎትን የ ምልክት አቀራረብ: በ ቅድሚያ የ ተገለጸ አቀራረብ ውስጥ የማይሸፈን: ይህን ለማድረግ: ይምረጡ "ተጠቃሚ" ከ አይነት ዝርዝር ሳጥን ውስጥ: ከ ምርጫ tab: እርስዎ መወሰን ይችላሉ ሁሉም ወይንም አንዳንድ ምልክቶች እንደሚፈጠሩ
ከ ምርጫ tab ገጽ ውስጥ: እርግጠኛ ይሁኑ የ ይዞታዎች ማስማሚያ ሳጥን መመረጡን: ይህ ከ ተመረጠ: ምልክት ብቻ መግባት አለበት (ከ ላይ በ ግራ ምልክት በኩል) እና አንዴ መታረም አለበት
ይጫኑ በ አዲስ ሰነድ ላይ ለ መፍጠር አዲስ ሰነድ እርስዎ ባስገቡት ማሰናጃዎች መሰረት
እርስዎ ወዲያውኑ እንደ ተጫኑ በ አዲስ ሰነድ ውስጥ: ለ እርስዎ ትንሽ መስኮት ይታያል በ ምልክቶች ማስማሚያ ቁልፍ ውስጥ: የ መጀመሪያውን ምልክት ያስገቡ: እርስዎ በሚጫኑ ጊዜ በ ምልክቶች ማስማሚያ ቁልፍ ውስጥ: የ አሁኑ እያንዳንዱ ምልክት ኮፒ ይደረጋል ወደ ሁሉም ሌሎች ምልክቶች በ ወረቀቱ ውስጥ