አቋራጮች (LibreOffice መድረሻ)

እርስዎ መቆጣጠር ይችላሉ LibreOffice ያለ አይጥ አካል: የ ፊደል ገበታ ብቻ በ መጠቀም

በ እያንዳንዱ ክፍሎች ዋናው የ እርዳታ ገጽ ውስጥ (ለምሳሌ: የ LibreOffice መጻፊያ ወይንም LibreOffice ሰንጠረዥ ዋናው የ እርዳታ ገጽ ውስጥ) አገናኝ አለ ለ መድረስ በ ፊደል ገበታ አቋራጮች ወደ እርዳታ ክፍል

በ ተጨማሪ በ ቁልፍ ቃል "መድረሻ" ስር: እርስዎ ያገኛሉ ደረጃ-በ-ደረጃ ትእዛዞች እንዴት እንደሚቆጣጠሩ ክፍሎችን ያለ አይጥ አካል

የ ማስታወሻ ምልክት

አንዳንድ አቋራጭ ቁልፎች በ እርስዎ የ ዴስክቶፕ ስርአት ውስጥ ተመድበው ይሆናል: ስለዚህ በ እርስዎ የ ዴስክቶፕ ውስጥ የ ተመደቡ አቋራጭ ቁልፎች ዝግጁ አይሆኑም ለ LibreOffice. ሌላ የ ተለየ ቁልፍ ለ መመደብ ይሞክሩ: ለ LibreOffice በ መሳሪያዎች - ማስተካከያ - የ ፊደል ገበታ ወይንም በ እርስዎ የ ዴስክቶፕ ስርአት ውስጥ


መስራት በ LibreOffice የ ተጠቃሚ ገጽታ ያለ አይጥ መጠቆሚያ

ዝርዝር መደርደሪያ: በ መስኮቶች እና በ ሰነድ ውስጥ ማስጀመሪያ

በ ተከታታይ መጫን F6 ትኩረቱን ይቀይራል እና በሚቀጥሉት እቃዎች ውስጥ ይዘዋወራል:

ይጫኑ Shift+F6 በ እቃዎች ውስጥ ለ መቀያየር በ ተቃራኒ አቅጣጫ

ይጫኑ +F6 በ ሰነድ ውስጥ ለ መቀየር

ይጫኑ F10 ለ መቀየር የ ዝርዝር መደርደሪያ እና ወደ ኋላ

መዝለያ ቁልፍ ይዘጋል የ ተከፈተ ንዑስ ዝርዝር: የ እቃ መደርደሪያ: ወይንም አሁን የ ተከፈተውን ነፃ መስኮት

ዝርዝር ትእዛዝ ለ መጥራት

ይጫኑ ወይንም F6 ወይንም F10 ለ መምረጥ የ መጀመሪያ ዝርዝር (የ ፋይል ዝርዝር). በ ቀኝ ቀስት: የሚቀጥለው ዝርዝር በ ቀኝ በኩል ያለው ይመረጣል: በ ግራ ቀስት ያለፈው ዝርዝር ይመረጣል

ቀስት ወደ ታች የ ተመረጠውን ዝርዝር ይከፍታል: ማንኛውም ተጨማሪ ቀስት ወደ ታች እና ቀስት ወደ ላይ በ ምርጫው ውስጥ ያንቀሳቅሳል በ ዝርዝር ትእዛዝች ውስጥ: በ ቀኝ ቀስት እርስዎ ማንኛውንም ንዑስ ዝርዝር መክፈት ይችላሉ

ይጫኑ ማስገቢያውን የ ተመረጠውን ዝርዝር ትእዛዝ ለ መፈጸም

የ ምልክት ትእዛዝ መፈጸሚያ

ይጫኑ F6 በ ተከታታይ የ መጀመሪያው ምልክት በ እቃ መደርደሪያ ላይ እስከሚመረጥ ድረስ: ይጠቀሙ የ ቀኝ ወይንም የ ግራ ቀስቶች ምልክት ለ መምረጥ በ አግድም ከ እቃ መደርደሪያ ላይ: በ ተመሳሳይ: የ ላይ ወይንም የ ታች ቀስቶች ምልክት ለ መምረጥ በ ቁመት ከ እቃ መደርደሪያ ላይ: የ ቤት ቁልፍ የሚመርጠው የ መጀመሪያውን ምልክት ነው በ እቃ መደርደሪያ ላይ እና የ መጨረሻ ቁልፍ የ መጨረሻውን ምልክት ነው

ይጫኑ ማስገቢያውን የ ተመረጠውን ምልክት ለ መፈጸም: የ ተመረጠው ምልክት በ ተከታታይ የ አይጥ ቁልፍ መጫን የሚፈልግ ከሆነ: እንደ አራት ማእዘን ማስገቢያ: እና ከዛ የ ማስገቢያ ቁልፍ መጫን ብቻ በቂ ላይሆን ይችላል: ይህ ሲያጋጥም ይጫኑ +ማስገቢያውን

የ እቃ መደርደሪያው መመልከቻው ሊያሳየው ከሚችለው በላይ ከሆነ: ምልክት ያሳያል በ ቀኝ በኩል ከ ታች ጠርዝ በኩል: የ እቃ መደርደሪያውን ይምረጡ እና ይጫኑ ገጽ ወደ ላይ ወይንም ገጽ ወደ ታች ቀሪውን ምልክቶች ለማሳየት

የ ተለየ ፍንጭ ለ እቃ መደርደሪያው

ይጫኑ ቀስት ወደ ታች ወይንም የ ቀኝ ቀስት የ ተመረጠውን የ እቃ መደርደሪያ ለ መክፈት: ይህ እኩል ነው ከ አይጥ መጫኛ ጋር: በ እቃ መደርደሪያው ላይ የ ቀኝ ቀስት ይጠቀሙ እና የ ግራ ቀስት ቁልፎች: የ ቤት እና መጨረሻ ቁልፎች የ መጀመሪያ እና የ መጨረሻ ምልክት ይመርጣሉ በ እቃ መደርደሪያው ላይ በትክክል:

የ እቃ መደርደሪያውን ይዝጉ በ Esc ቁልፍ: የ እቃ መደርደሪያውን ማንቀሳቀስ ካልተቻለ ያለ አይጥ መጠቆሚያ

ከ መቀላቀያ ሳጥን ውስጥ መምረጫ

መቀላቀያ ሳጥን

ይምረጡ መቀላቀያ ሳጥን: እና ይጫኑ ማስገቢያውን

ይጠቀሙ ቀስት ወደ ታች ወይንም ቀስት ወደ ላይ ቁልፍ ወደ ታች ለ መሸብለል በ መቀላቀያ ሳጥን ማስገቢይ ውስጥ: ወይንም ቀስት ወደ ላይ ወይንም ገጽ ወደ ላይ ወደ ላይ ለ መሸብለል: የ ቤት ቁልፍ ወደ መጀመሪያው ማስገቢያ ይወስዶታል: እና የ መጨረሻ ቁልፍ ወደ መጨረሻው ማስገቢያ ይወስዶታል:

የ ተመረጠውን ማስገቢያ ለ መፈጸም ይጫኑ ማስገቢያውን

በ ሰንጠረዥ ውስጥ መምረጫ

በ በርካታ መስኮቶች: ንግግሮች: እና የ ሰንጠረዥ መቆጣጠሪያ ሜዳ ውስጥ: እርስዎ ዳታ የሚመርጡበት ሰንጠረዦች አሉ: ለምሳሌ: የ ቀኝ ክፍል ለ ዳታ ምንጭ መመልከቻ የሚቀጥሉትን ቁልፎች ይጠቀሙ ለ መምረጫ ከ እነዚህ ሰንጠረዦች ውስጥ:

የ መስኮቶች እና ንግግሮች መጠን እና ቦታ

  1. መጀመሪያ ይጫኑ +የ ክፍተት ማስገቢያ ቁልፍ

    የ ስርአቱ ዝርዝር ይከፈታል ከ ዝርዝር ትእዛዞች ጋር እንደ ማንቀሳቀሻ እንደገና መመጠኛ እና መዝጊያ.

  2. ትእዛዝ ይምረጡ (ቀስት ወደ ታች: ማስገቢያ)

  3. እርስዎ አሁን የ ቀስት ቁልፎች መጠቀም ይችላሉ ለ ማንቀሳቀስ: ወይንም ንግግር ወይንም መስኮት እንደገና ለ መመጠን

  4. ይጫኑ ማስገቢያ ለውጦቹን ለ መቀበል: ይጫኑ መዝለያውን ለውጦቹን ለ መሰረዝ

መስኮቶች እና የ እቃ መደርደሪያ ማሳረፊያ እና ማባረሪያ

  1. ይጫኑ F6 መስኮት ወይንም እቃ መደርደሪያ እስከሚመረጥ ድረስ

  2. ይጫኑ +Shift+F10.

እቃዎችን መምረጫ

ይጫኑ Shift+F4 የ መጀመሪያውን እቃ ለ መምረጥ ከ አሁኑ ሰነድ ውስጥ: እቃው ሲመረጥ: ይጫኑ Tab የሚቀጥለውን እቃ ለ መምረጥ: ወይንም ይጫኑ Esc ወደ ጽሁፉ ለ መመለስ

እቃዎች ማረሚያ

የ ተመረጠውን የ OLE እቃ ማስጀመር ይቻላል ማስገቢያ ቁልፍ በ መጫን

የ እቃዎች መጠን እና ቦታ ማረሚያ

የ እቃዎች ማስቆሚያ ማረሚያ

እርስዎ ማንቀሳቀስ ይችላሉ የ እቃ ማስቆሚያ በ ቀስት ቁልፎች: መጀመሪያ ወደ ማረሚያ ዘዴ እጄታ ይግቡ እና ይምረጡ ማስቆሚያ: እንደ ማስቆሚያው አይነት: እርስዎ ማስቆሚያውን ማንቀሳቀስ ይችላሉ በ ተለያየ አቅጣጫ

  1. እቃ ይምረጡ

  2. ወደ ማረሚያ ዘዴ እጄታ መግቢያ በ +Tab.

  3. የ ላይኛው የ ግራ ንቁ እጄታ: ብልጭ ድርግም ማለት ይጀምራል: ይጫኑ +Tab በርካታ ጊዜ: እጄታ: ብልጭ ድርግም ማለት እስኪያቆም: ይህ ለ እርስዎ ምልክት ነው የ ማስቆሚያው እቃ መጀመሩን

  4. ማስቆሚያውን ለማንቀሳቀስ የ ቀስት ቁልፎች ይጠቀሙ: እቃው ማስቆሚያውን ይከተላል

እርስዎ የ ተመረጠውን እቃ ማስቆሚያ መቀየር ይችላሉ: ለምሳሌ: በ እቃዎች አገባብ ዝርዝር ውስጥ

የ መከፋፈያ መስመሮች መቆጣጠሪያ

ሰነዶች የ LibreOffice ሰንጠረዥ LibreOffice መሳያ እና LibreOffice ማስደነቂያ መክፈል ይቻላል በ አግድም እና በ ቁመት ወደ ተለያየ መመልከቻዎች ውስጥ: እያንዳንዱ መመልከቻ የ ሰነዱን የ ተለያየ ክፍል ማሳየት ይችላል: የ አይጥ ቁልፍ በ መጠቀም: እርስዎ መጎተት ይችላሉ የ መከፋፈያ መስመር ከ መሸብለያ መደርደሪያ ላይ በ ሰነድ ውስጥ

የ ዳታ ምንጭ መመልከቻ መቆጣጠሪያ

+ Shift + F4 መክፈቻ እና መዝጊያ የ ዳታ ምንጭ መመልከቻ

F6: በ ሰነድ እና በ እቃ መደርደሪያ መካከል መቀያየሪያ

+ (መደመሪያ ቁልፍ): የ ተመረጠውን ማስገቢያ ያሰፋል ለ ዳታ ምንጭ መቃኛ

- (መቀነሻ ቁልፍ): የ ተመረጠውን ማስገቢያ ያሳንሳል ለ ዳታ ምንች

+Shift+E: ከ ዳታ ምንጭ መቃኛ እና ሰንጠረዥ ውስጥ ለ መቀያየር

አቋራጮች በ ጥያቄ ንድፍ መስኮት ውስጥ

F6: በ እቃ መደርደሪያ: በ ሰንጠረዥ መመልከቻ: እና በ ተመረጠው ቦታ መካከል መቀያየሪያ

+ቀስት ወደ ላይ ወይንም +ቀስት ወደ ታች: ያንቀሳቅሳል በ ሰንጠረዥ መመልከቻውን እና የ መምረጫ ቦታ ወደ ላይ ወይንም ወደ ታች በ ድንበር መካከል

ቁልፎች በ ሰንጠረዥ መመልከቻ ውስጥ (በ ጥያቄ ንድፍ ውስጥ ከ ላይ በኩል) እና ከ መስኮቱ ግንኙነት

+የ ቀስት ቁልፍ: የ ተመረጠውን ሰንጠረዥ በ ቀስቱ አቅጣጫ ያንቀሳቅሳል

+Shift+የ ቀስት ቁልፍ የ ተመረጠውን ሰንጠረዥ በ ሰንጠረዥ መመልከቻ እንደገና ይመጥናል

ማጥፊያ: የ ተመረጠውን ሰንጠረዥ ወይንም ግንኙነት ከ ሰንጠረዥ መመልከቻ ላይ ማስወገጃ

Tab: በ ሰንጠረዥ እና በ ሰንጠረዥ ግንኙነቶች መመልከቻ መካከል መቀያየሪያ

ማስገቢያ: ግንኙነት ሲመረጥ: የ ማስገቢያ ቁልፍ ይክፍታል የ ባህሪዎችንግግር ለ ግንኙነት

ማስገቢያ: ሰንጠረዥ በሚመረጥ ጊዜ: የ ማስገቢያ ቁልፍ ያስገባል የ መጀመሪያውን ዳታ ሜዳ ከ ዝርዝር ሳጥን ውስጥ ወደ ተመረጠው ቦታ

ቁልፎች በ ምርጫ ቦታ (በ ጥያቄ ንድፍ ከ ታች በኩል)

+የ ግራ ቀስት ወይንም የ ቀኝ ቀስት: የ ተመረጠውን አምድ ወደ ግራ ወይንም ወደ ቀኝ ያንቀሳቅሳል

ቁልፎች በ ሰንጠረዥ ንድፍ መስኮት ውስጥ

F6: በ እቃ መደርደሪያ: በ አምድ መመልከቻ: እና በ ባህሪዎች ቦታ መካከል መቀያየሪያ

የ ምስል ካርታ ማረሚያ መቆጣጠሪያ

እርዳታ መቆጣጠሪያ

ይጫኑ Shift+F1 ለማሳየት የ ተስፋፉ ምክሮች አሁን ለተመረጠው ትእዛዝ: ምልክት ወይንም መቆጣጠሪያ

ዋናውን የ እርዳታ ገጾች መቃኛ

መቆጣጠሪያ የ ጽሁፍ ማምጫ ንግግር (CSV ፋይል ማምጫ)

ማስመሪያ

ቅድመ እይታ

የ ተለዩ ባህሪዎች ንግግር - ማስገቢያ መቆጣጠሪያ

Please support us!