የ ንድፍ እቃዎች ማረሚያ

ይምረጡ መመልከቻ - እቃ መደርደሪያ - መሳያ ለ መክፈት የ መሳያ እቃ መደርደሪያ: ቀደም ብሎ ካልተከፈተ

እቃዎችን መሳል: ማረም: እና ማሻሻል ይቻላል: በዚህ ዘዴ የ ተፈጠረ ንድፍ የ አቅጣጫ ንድፍ ይባላል: እርስዎ መጠኑን ጥራቱ ሳይጎድል መቀየር ይችላሉ

አራት ማእዘን ለ መፍጠር: ይጫኑ በ አራት ማእዘን ምልክት ላይ እና የ አይጥ መጠቆሚያውን ወደ ሰነዱ ውስጥ ያንቀሳቅሱ: እርስዎ አንዱ የ አራት ማእዘን ጠርዝ እንዲጀምር በሚፈልጉበት ቦታ እና ይጫኑ የ አይጥ ቁልፍ እና ተጭነው ይያዙ እና ከዛ ይጎትቱ ወደ ተቃራኒው ጠርዝ በኩል: እርስዎ አይጡን በሚለቁ ጊዜ: አራት ማእዘን በ ሰነዱ ውስጥ ይገባል: እና የ ተመረጠ ነው: ስለዚህ እርስዎ ባህሪዎቹን በ አገባብ ዝርዝር ማረም ይችላሉ

note

ወደ መደበኛ ዘዴ ለ መቀየር የ መሳያ እቃዎች ከ ፈጠሩ እና ካረሙ በኋላ: ይጫኑ በ ሰነዱ ላይ ምንም እቃ በሌለበት ቦታ ላይ: ለ እርስዎ የ መሳያ መጠቆሚያ ከታየዎት: በ መጀመሪያ ከዚህ ዘዴ ውስጥ ይውጡ: በ መጫን የ መምረጫ ምልክት


Please support us!