LibreOffice 7.6 እርዳታ
በ ቀጥታ ፋክስ ለ መላክ ከ LibreOffice እርስዎ ያስፈልጎታል የ ፋክስ ሞደም: እና የ ፋክስ driver መተግበሪያዎችን መገናኘት የሚያስችል ከ ፋክስ ሞደም ጋር
መክፈቻ የ ማተሚያ ንግግር በመምረጥ ፋይል - ማተሚያ እና ይምረጡ ማተሚያውን ከ ስም ዝርዝር ሳጥን ውስጥ
ከ ተጫኑ እሺ ንግግር ይከፈታል ለ ፋክስ driver: የ ፋክሱን ተቀባይ የሚመርጡበት
እርስዎ ማዋቀር ይችላሉ LibreOffice ስለዚህ አንድ ጊዜ ሲጫኑ በ ምልክቱ ላይ ራሱ በራሱ የ አሁኑን ሰነድ እንደ ፋክስ አንዲልክ:
ይምረጡ - LibreOffice መጻፊያ - ማተሚያ
ይምረጡ የ ፋክስ driver ከ ፋክስ ዝርዝር ሳጥን ውስጥ እና ይጫኑ እሺ
ይጫኑ የ ቀስት ምልክት ከ ታች ያለውን ከ መደበኛ እቃ መደርደሪያ ውስጥ ወደ ታች-የሚዘረገፈውን ዝርዝር ይምረጡ ማስተካከያ
የ እቃ መደርደሪያ tab ገጽ የ ማስተካከያ ንግግር ይታያል
ይጫኑ ትእዛዝ መጨመሪያ
ይምረጡ የ "ሰነዶች" ምድብ ከዛ ይምረጡ የ "ነባር ፋክስ መላኪያ" ትእዛዝ
ይጫኑ መጨመሪያ እና ከዛ መዝጊያ
በ እቃ መደርደሪያ tab ገጽ ውስጥ ይጫኑ ቀስት ወደ ታች ቁልፍ አዲሱን ምልክት ማስቀመጥ የሚፈልጉበት ቦታ እና ይጫኑ እሺ
የ እርስዎ መደበኛ መደርደሪያ አሁን አዲስ ምልክት አለው የ አሁኑን ሰነድ እንደ ፋክስ ለ መላኪያ