ዳታ በ ጽሁፍ አቀራረብ ማምጫ እና መላኪያ

እርስዎ ከ ፈለጉ ዳታ መቀያየር ከ ዳታቤዝ ጋር የ ODBC አገናኝ የሌለው እና የ ዳታቤዝ ማምጣት እና መላክ የማይፈቅድ: እርስዎ መጠቀም ይችላሉ መደበኛ የ ጽሁፍ አቀራረብ

ዳታ ማምጫ ወደ LibreOffice

በ ጽሁፍ አቀራረብ ዳታ ለ መቀያየር የ LibreOffice ሰንጠረዥ ማምጫ/መላኪያ ማጣሪያ ይጠቀሙ

  1. የ ተፈለገውን ዳታ መላኪያ ከ ዳታቤዝ ምንጭ ውስጥ በ ጽሁፍ አቀራረብ: የ CSV ጽሁፍ አቀራረብ እንዲጠቀሙ ይመከራሉ: ይህ አቀራረብ የ ዳታ ሜዳዎች ይለያያል በ መጠቀም ስርአተ ነጥብ እንደ ኮማ ወይንም ሴሚ-ኮለን እና መዝገቦችን ይለያያል የ መስመር መጨረሻ በማስገባት

  2. ይምረጡ ፋይል - መክፈቻ እና ይጫኑ የሚመጣውን ፋይል

  3. ይምረጡ "Text CSV" ከ ፋይል አይነት መቀላቀያ ሳጥን ውስጥ: ይጫኑ መክፈቻ

  4. ጽሁፍ ማምጫ ንግግር ይታያል: ከ ጽሁፍ ሰነድ ውስጥ የትኛው ዳታ እንደሚካተት ይወስኑ

አንዴ ዳታ ከ ገባ በ LibreOffice ሰንጠረዥ ውስጥ: እርስዎ ማረም ይችላሉ እንደፈለጉ: ዳታውን ያስቀምጡ እንደ የ LibreOffice ዳታ ምንጭ:

በ CSV ጽሁፍ አቀራረብ መላኪያ

እርስዎ መላክ ይችላሉ LibreOffice ሰንጠረዥ በ ጽሁፍ አቀራረብ በ ሌሎች መተግበሪያውች በ ቀላሉ እንዲነበብ

  1. ይምረጡ ፋይል - ማስቀመጫ እንደ

  2. ፋይል አይነት ውስጥ ይምረጡ የ ማጣሪያ "Text CSV". የ ፋይል ስም ያስገቡ እና ይጫኑ ማስቀመጫ

  3. ይህ መክፈቻ የ ጽሁፍ ፋይሎች መላኪያ ንግግር ነው: እርስዎ መምረጥ የሚችሉበት የ ባህሪ ማሰናጃ: የ ሜዳዎች ክፍተት እና ክፍተት: ይጫኑ እሺ ማስጠንቀቂያ ይታይዎታል ንቁ ወረቀት ብቻ እንደተቀመጠ

Please support us!