ለ ሰንጠረዥ እና ለ ሰንጠረዥ ክፍሎች ድንበሮች መግለጫ

በ ቅድሚያ የተገለጹ የ ድንበር ዘዴዎች ማስናጃ

  1. ማሻሻል የሚፈልጉትን የ ሰንጠረዥ ክፍል ይምረጡ

  2. ይጫኑ የ ድንበሮች ምልክት ከ ሰንጠረዥ እቃ መደርደሪያ (መጻፊያ) ወይንም ከ መስመር እና መሙያ መደርደሪያ ላይ ለ መክፈት የ ድንበሮች መስኮት

  3. ይጫኑ አንዱን በ ቅድሚያ የ ተገለጸ የ ድንበር ዘዴ

    ይህ መጨመሪያ የ ተመረጠውን ዘዴ ወደ አሁኑ የ ድንበር ዘዴ ለ ሰንጠረዥ ክፍሎች ያስገባል: ይምረጡ ባዶ የ ድንበር ዘዴ ከ ላይ በ ግራ በኩል ከ ድንበሮች መስኮት ውስጥ የ ድንበር ዘዴዎችን ለ ማጽዳት

የ ድንበር ዘዴ ማሰናጃ ማስተካከያ

  1. ማሻሻል የሚፈልጉትን የ ሰንጠረዥ ክፍል ይምረጡ

  2. ይምረጡ ሰንጠረዥ - ባህሪዎች - ድንበሮች (መጻፊያ) ወይንም አቀራረብ - ክፍሎች - ድንበሮች (ሰንጠረዥ)

  3. ተጠቃሚ-የሚገለጽ ቦታ ይምረጡ ጠርዝ(ዞች) በ መደበኛ ቦታ እንዲታይ የሚፈልጉትን: ይጫኑ በ ጠረዙ ላይ በ ቅድመ እይታ መመልከቻ ላይ የ ጠርዝ ምርጫውን ለ መቀያየር

  4. እርስዎ ከ አንድ በላይ ረድፍ ወይንም አምድ ከ መረጡ: እርስዎ መቀየር ይችላሉ በ ረድፍ ወይንም በ አምድ መካከል ያሉትን መስመሮች: ይምረጡ መሀከል ምልክት ማድረጊያ በ ተጠቃሚ-የሚገለጽ ቦታ ውስጥ

  5. ይምረጡ የ መስመር ዘዴ እና ቀለም ለ ተመረጠው የ ድንበር ዘዴ ከ መስመር ቦታ: ይህ ማሰናጃ ይፈጸማል ለ ሁሉም የ ድንበር መስመሮች በ ተመረጠው የ ድንበር ዘዴ ውስጥ ለሚካተቱት ሁሉ

  6. የ መጨረሻውን ሁለት ደረጃዎች ይድገሙ ለ እያንዳንዱ ድንበር ጠርዝ

  7. ይምረጡ እርቀት በ ድንበር መስመር እና በ ገጽ ይዞታ መካከል በ መጨመሪያ ቦታ ውስጥ

  8. ይጫኑ እሺ ለውጦቹን ለ መፈጸም

Please support us!