LibreOffice 24.8 እርዳታ
ይህ አዋቂ የ አጄንዳ ቴምፕሌት ለ መፍጠር ይረዳዎታል እርስዎ ይህን አጄንዳ የ ውይይት አርእስቶች ለ መወሰን መጠቀም ይችላሉ ለ ውይይት እና ስብሰባዎች
LibreOffice ከ አጄንዳ ሰነዶች ቴምፕሌት ጋር አብሮ ይመጣል: እርስዎ ማሻሻል ይችላሉ በ አዋቂው የ እርስዎን ፍላጎት እንዲያሟላ አድርገው: አዋቂው ይመራዎታል የ ሰነድ ቴምፕሌት ለ መፍጠር: እና በርካታ እቅድ: የ ንድፍ ምርጫዎች ያቀርባል: የ ሰነድ ቅድመ እይታ ፋክሱ ምን እንደሚመስል በ ቅድሚያ ያሳይዎታል
በ አዋቂው እርስዎ በማንኛውም ጊዜ የ እርስዎን ማስገቢያ እና ምርጫ ማሻሻል ይችላሉ: ጠቅላላ ገጽ መዝለል ይችላሉወይንም ባጠቃላይ የ አዋቂውን ገጽ መዝለል ይችላሉ: የ አሁኑ (ወይንም ነባር) ማሰናጃው እንደ ነበር ውጤቱ ይቆያል
ባለፈው ገጽ የ ተመረጠውን ይመልሳል: የ አሁኑ ማሰናጃ እንደ ነበር ይቆያል: ይህ ገጽ ዝግጁ የሚሆነው ከ መጀመሪያው ገጽ በኋላ ነው
አዋቂው የ አሁኑን ማሰናጃ ያስቀምጣል እና ወደሚቀጥለው ገጽ ይሄዳል: መጨረሻው ገጽ ላይ ሲደርሱ ይህ ቁልፍ ንቁ አይሆንም
እንደ እርስዎ ምርጫ አይነት: አዋቂው የ ሰነድ ቴምፕሌት ይፈጥር እና ያስቀምጣል በ እርስዎ ሀርድ ዲስክ ላይ: አዲስ ሰነድ ቴምፕሌቱን መሰረት ያደረገ በ ስራ ቦታ ላይ ይታያል: በ ፋይል ስም "ያልተሰየመX" (X የሚወክለው ራሱ በራሱ ቁጥር መስጫ ነው)
LibreOffice የ አሁኑን የ አዋቂውን ማሰናጃዎች ያስቀምጣል: እንደ ተመረጠው ቴምፕሌት: እነዚህን ማሰናጃዎች ይጠቀማል እንደ ነባር ማሰናጃ በሚቀጥለው ጊዜ አዋቂው ሲያስጀምሩ