መፈለጊያ - የ ሙሉ-ጽሁፍ መፈለጊያ

የ ሙሉ ጽሁፍ መፈለጊያ ተግባር በ LibreOffice እርዳታ ውስጥ እርስዎን የሚያስችለው የ እርዳታ ሰነዶች ፈልገው እንዲያገኙ ነው: ማንኛውንም የሚፈለገውን ቃል የያዘ: ይህን ለማድረግ: ይጻፉ አንድ ወይንም ከዚያ በላይ ቃሎች ወደ መፈለጊያ ደንብ ጽሁፍ ሜዳ ውስጥ

መፈለጊያ ደንብ ጽሁፍ ሜዳ ያስቀምጣል እርስዎ መጨረሻ ያስገቡትን ቃል: ያለፈውን ፍለጋ ለ መድገም: ይጫኑ የ ቀስት ቁልፍ ምልክት እና ይምረጡ የሚፈልጉትን ደንብ ከ ዝርዝር ውስጥ

ፍለጋው ከ ተካሄደ በኋላ የ ሰነዱ ራስጌ ውጤት ይታያል በ ዝርዝር ውስጥ: ሁለት ጊዜ-ይጫኑ በ ውጤቱ ላይ ወይንም ይምረጡት እና ይጫኑ ማሳያ ተመሳሳዩን የ እርዳታ ገጽ ለ መጫን

ምልክት ማድረጊያውን ሳጥን ይጠቀሙ ራስጌዎች ብቻ መፈለጊያ ለ ራስጌ ሰነድ ብቻ መፈለጊያ ለመወሰን

ሙሉ ቃሎች ብቻ ምልክት ማድረጊያ ሳጥን እርስዎን የሚያስችለው በ ትክክል ቃሉን መፈለግ ነው: ይህ ሳጥን ምልክት ከ ተደረገበት: ያልተሟሉ ቃሎች አይገኙም: በዚህ ሳጥን ውስጥ ምልክት አያድርጉ: እርስዎ ያስገቡት የ መፈለጊያ ደንብ እንደ እረጅም ቃል አብሮ እንዲፈለግ

እርስዎ ማስገባት ይችላሉ ማንኛውንም የ መቀላቀያ መፈለጊያ ደንብ: በ ክፍተት ለያይተው: መፈለጊያ ፊደል-መመጠኛ አይደለም

የ ምክር ምልክት

ይህ ማውጫ እና ሙሉ-ጽሁፍ መፈለጊያ ሁልጊዜ ይፈጸማል በ አሁን በ ተመረጠው LibreOffice መተግበሪያ ውስጥ: ይምረጡ ተገቢውን መተግበሪያ የ ዝርዝር ሳጥን በ መጠቀም በ እርዳታ መመልከቻ እቃ መደርደሪያ ላይ


Please support us!