LibreOffice 25.2 እርዳታ
የ ማቅረቢያ መደርደሪያ ይታያል ወደ ቻርትስ ማረሚያ ዘዴ ሲገቡ: ሁለት-ጊዜ ይጫኑ በ ቻርትስ ላይ ወደ ማረሚያ ዘዴ ለመግባት: ከ ቻርትስ ውጪ ይጫኑ ከ ማረሚያ ዘዴ ለ መውጣት
እርስዎ የ ቻርትስ አቀራረብ ማረም ይችላሉ መቆጣጠሪያዎች እና ምልክት በ መጠቀም በ አቀራረብ መደርደሪያ ላይ
ይምረጡ አካል ከ ቻርትስ ውስጥ እርስዎ ማቅረብ የሚፈልጉትን: አካሉ ይመረጣል በ ቻርትስ ቅድመ እይታ መመልከቻ ውስጥ: ይጫኑ የ አቀራረብ ምርጫ የ ባህሪዎችን ንግግር ለ መክፈት ለ ተመረጠው አካል
ለ ተመረጠው አካል ባህሪዎች መክፈቻ
የ ቻርት አይነት ንግግር መክፈቻ
የ ቻርትስ ዳታ የሚያርሙበት የ ዳታ ሰንጠረዥ ንግግር መክፈቻ
የ አግድም መጋጠሚያ ምልክት በ አቀራረብ መደርደሪያ ላይ መመልከቻውን ይቀያይራል የ መጋጠሚያ ማሳያውን ለ Y አክሲስ
መግለጫውን ለ ማሳየት ወይንም ለ መደበቅ: ይጫኑ መግለጫ ማብሪያ/ማጥፊያ በ አቀራረብ መደርደሪያ ላይ
እርስዎ የ ቻርት መጠን በሚቀይሩ ጊዜ ጽሁፉን እንደገና መመጠኛ
በ አሁኑ የ ቻርትስ ሰነድ ውስጥ ሁሉንም የ ቻርትስ አካላቶች ወደ ነባር ቦታቸው መመለሻ: ይህ ተግባር የ ቻርትስ አይነቱን ወይንም ሌሎች ባህሪዎች አይቀይርም ከ አካላቶቹ ቦታ በስተቀር