ቻርትስ አጠቃቀም በ LibreOffice

External video

Please accept this video. By accepting you will be accessing content from YouTube, a service provided by an external third party.

YouTube Privacy Policy

LibreOffice እርስዎን ዳታ በ ቻርትስ ውስጥ በ ንድፍ ዘዴ ማቅረብ እና ማየት ያስችሎታል: ስለዚህ እርስዎ ተከታታይ ዳታ ማወዳደር እና የ ዳታ አቅጣጫን ማየት ይችላሉ: እርስዎ ቻርትስ ወደ ሰንጠረዦች: የ ጽሁፍ ሰነዶች: መሳያዎች እና ማቅረቢያዎች ውስጥ ማስገባት ይችላሉ

የ ቻርትስ ዳታ

ቻርትስ የሚቀጥለውን ዳታ መሰረት ያደረገ ሊሆን ይችላል:

 1. የ ሰንጠረዥ ዋጋዎች ከ ሰንጠረዥ ክፍል መጠኖች ውስጥ

 2. የ ክፍል ዋጋ በ መጻፊያ ሰንጠረዥ ውስጥ

 3. እርስዎ ያስገቡዋቸው ዋጋዎች በ ቻርትስ ዳታ ሰንጠረዥ ንግግር ውስጥ: (እርስዎ መፍጠር ይችላሉ እነዚህን ቻርትስ በ መጻፊያ: በ መሳያ: ወይንም ማስደነቂያ: እና ኮፒ አድርገው መለጠፍ ይችላሉ ወደ ሰንጠረዥ ውስጥ)

ቻርትስ ለማስገባት

የ ቻርትስ ማስገቢያ

የ ቻርትስ አይነት መምረጫ

ቻርትስ ለማረም

 1. ይጫኑ በ ቻርትስ ላይ የ እቃውን ባህሪ ለማረም:

  በአሁኑ ገጽ ላይ መጠኑ እና ቦታው

  ማሰለፊያ፡ ጽሁፍ መጠቅለያ፡ የውጪ ድንበሮች እና ተጨማሪ

 2. ሁለት-ጊዜ ይጫኑ በ ቻርትስ ላይ ወደ ቻርትስ ማረሚያ ዘዴ ለመግባት:

  የ ቻርትስ ዳታ ዋጋዎች (ለ ቻርትስ ከ ራሱ ዳታ ጋር)

  የ ቻርትስ አይነት: አክሲስ: አርእስቶች: ግድግዳዎች: መጋጠሚያዎች: እና ተጨማሪዎች

 3. ሁለት-ጊዜ ይጫኑ በ ቻርትስ አካል ላይ ወደ ቻርትስ ማረሚያ ዘዴ ለመግባት:

  ሁለት-ጊዜ ይጫኑ በ አክሲስ ላይ መጠን: አይነት: ቀለም እና ተጨማሪዎች ለማረም

  ሁለት-ጊዜ ይጫኑ የ ዳታ ነጥብ ላይ ለ መምረጥ እና ለማረም ተከታታይ ዳታ: የ ዳታው ነጥብ የሚገኝበት ቦታ

  ተከታታይ ዳታ ከ ተመረጠ በኋላ: ይጫኑ ሁለት ጊዜ-ይጫኑ በ ነጠላ ዳታ ነጥብ ላይ ባህሪውን ለ ማረም የዚህን ዳታ ነጥብ (ለምሳሌ ነጠላ መደርደሪያ በ ቻርትስ መደርደሪያ ላይ)

  ሁለት-ጊዜ ይጫኑ በ መግለጫ ላይ ለ መምረጥ እና ለማረም: ይጫኑ እና ከዛ ሁለት-ጊዜ ይጫኑ በ ተመረጠው መግለጫ ምልክት ላይ የተዛመደውን ተከታታይ ዳታ ለማረም

  ሁለት-ጊዜ ይጫኑ በ ሌላ ቻርትስ አካል ላይ: ወይንም ይጫኑ አካሉን እና ይክፈቱ የ አቀራረብ ዝርዝር ባህሪዎችን ለማረም

 4. ከ ቻርትስ ውጪ ይጫኑ ከ ማረሚያ ዘዴ ለመውጣት

የ ምክር ምልክት

ቻርት በ ከፍተኛ ጥራት ለማተም: እርስዎ ቻርት መላክ ይችላሉ ወደ PDF ፋይል እና ፋይሉን ማተም ይችላሉ


በ ቻርት ማረሚያ ዘዴ ውስጥ: ለ እርስዎ ይታያል የ አቀራረብ መደርደሪያ ለ ቻርትስ በ ሰነዱ ውስጥ ከ ላይ በኩል ይታያል: የ መሳያ መደርደሪያ ለ ቻርትስ በ ሰነዱ ውስጥ ከ ታች በኩል ይታያል: የ መሳያ መደርደሪያ የሚያሳየው ንዑስ ስብስብ ምልክት ነው ለ መሳያ እቃ መደርደሪያ ለ መሳያ እና ማስደነቂያ

ሁለት-ጊዜ ይጫኑ በ ቻርትስ አካል ላይ: ወይንም ይጫኑ አካሉን እና ይክፈቱ የ አገባብ ዝርዝር: የ አገባብ ዝርዝር ለሚመረጠው አካል አቀራረብ በርካታ ትእዛዞችን ይዟል

የ ቻርትስ አርእስቶች ማረሚያ

የ ቻርትስ አክሲስ ማረሚያ

የ ቻርትስ መግለጫዎች ማረሚያ

ገጽታ መጨመሪያ ወደ ቻርትስ መደርደሪያ ላይ

3ዲ መመልከቻ

እርዳታ ስለ እርዳታ

የ እርዳታ ማመሳከሪያ ነባር ማሰናጃዎች ለ ፕሮግራም በ ስርአት ውስጥ እንደ ነባር ከ ተሰናዳ: የ ቀለሞች መግለጫ: የ አይጥ ተግባሮች: ወይንም ሌሎች ማሰናጃ እቃዎች ልዩ ሊሆኑ ይችላሉ ከ እርስዎ ፕሮግራም እና ስርአት ጋር

Please support us!