X/Y ስህተት መደርደሪያ

ይጠቀሙ የ X ወይንም Y ስህተት መደርደሪያዎች ንግግር ለማሳየት የ ስህተት መደርደሪያ ለ 2ዲ ቻርትስ

የ ተከታታይ አካል ዳታ ከ ተመረጠ : ይህ ትእዛዝ በ ተመረጠው ተከታታይ ዳታ ላይ ብቻ ይሰራል: ምንም አካል ካልተመረጠ ይህ ዳታ በ ሁሉም ተከታታይ ዳታ ላይ ይሰራል

ይህን ትእዛዝ ለ መፈጸም...

ይምረጡ ማስገቢያ - የ X ስህተት መደርደሪያ, or ማስገቢያ - የ Y ስህተት መደርደሪያ (ቻርትስ)


የ ስህተት መጠቆሚያ መስመር ክፍተት መጠን ስፋት በ x/y – የ አሉታዊ የ ስህተት ዋጋ ለ x/y + የ አዎንታዊ የ ስህተት ዋጋ: በዚህ ደንብ: x ወይንም y ዋጋ ነው ለ ዳታ ነጥብ: ይህ "standard deviation" ይመረጣል x ወይንም y መካከለኛ ነው ለ ታከታታይ ዳታ: የ አሉታዊ የ ስህተት ዋጋ እና የ አዎንታዊ የ ስህተት ዋጋ ናቸው ለ መጠኖች ማስሊያ በ ስህተት መደርደሪያ ተግባር ወይንም የ ተሰጠው በ ሙሉ

የ ማስታወሻ ምልክት

ማስገቢያ - X/Y ስህተት መደርደሪያ ዝርዝር ትእዛዝ ዝግጁ የሚሆነው ለ 2ዲ ቻርትስ ብቻ ነው


የ ስህተት ምድብ

ስህተት ምድብ ቦታ ውስጥ: እርስዎ መምረጥ ይችላሉ ለ ስህተት ምድብ የ ተለያዩ ማሳያዎችን

ምንም

ምንም የ ስህተት መደርደሪያ አያሳይም

የማያቋርጥ ዋጋ

መደበኛ ዋጋ ማሳያ እርስዎ የወሰኑትን በ ደንቦች ቦታ ውስጥ

ፐርሰንት

ፐርሰንቴጅ ማሳያ: ማሳያው የሚያመሳክረው ለ ተመሳሳይ ዳታ ነጥብ ነው: ፐርሰንቴጅ በ ደንቦች ቦታ ማሰናጃ ውስጥ

ተግባሮች

የ ስህተት መደርደሪያ ለማስላት ተግባር ይምረጡ

መደበኛ ስህተት: የሚያሳየው መደበኛ ስህተት ነው

ልዩነቶች: የሚያሳየው ልዩነቶች ነው የ ተሰላውን ከ ቁጥር ውስጥ የ ዳታ ነጥቦች እና ተመሳሳይ ዋጋዎች

መደበኛ ልዩነት: የሚያሳየ የ መደበኛ ልዩነት ነው (ስኴር ሩት ለ ልዩነት) ከ ሌሎች ተግባሮች በተለየ: የ ስህተት መደርደሪያ መሀከል ይሆናል እንደ አማካይ

የ ስህተት መስመር: የሚያሳየው ከፍተኛውን የ ስህተት መስመር ነው በ ፐርሰንት ከ ከፍተኛው ዋጋ የ ዳታ ቡድን ውስጥ: በ ደንቦች ቦታ ፐርሰንቴጅ ያሰናዱ

የክፍል መጠን

ይጫኑ የ ክፍል መጠን ላይ እና ከዛ ይወስኑ የ ክፍል መጠን እርስዎ የ አዎንታዊ እና አሉታዊ የ ስህተት መደርደሪያ ዋጋዎች የሚወስዱበት

ከ ዳታ ሰንጠረዥ

የ ራሱ ዳታ ላለው ቻርትስ: የ ስህተት መደርደሪያ ዋጋዎች ማስገባት ይቻላል በ ቻርትስ ዳታ ሰንጠረዥ ውስጥ: የ ዳታ ሰንጠረዥ ንግግር የሚያሳየው ተጨማሪ የ አምዶች አርእስት አዎንታዊ X ወይንም Y-የ ስህተት-መደርደሪያ እና አሉታዊ የ X ወይንም የ Y-ስህተት-መደርደሪያ ነው

እኩል ዋጋ ለሁለቱም

ያስችሉ ለ መጠቀም የ አዎንታዊ ስህተት ዋጋዎች እንዲሁም የ አሉታዊ ስህተት ዋጋዎች: እርስዎ መቀየር የሚችሉት የ "አዎንታዊ (+)" ሳጥን ብቻ ነው: ዋጋው ኮፒ ይደረጋል ወደ የ "አሉታዊ (-)" ሳጥን ውስጥ ራሱ በራሱ

ስህተት መጠቆሚያ

የ ስህተት መጠቆሚያ መወሰኛ

አዎንታዊ እና አሉታዊ

የ አዎንታዊ እና አሉታዊ ስህተት መደርደሪያ ማሳያ

አዎንታዊ

የ አዎንታዊ ስህተት መደርደሪያ ብቻ ማሳያ

አሉታዊ

የ አሉታዊ ስህተት መደርደሪያ ብቻ ማሳያ

Please support us!