ቁጥሮች እንደ ጽሁፍ ማቅረቢያ

እርስዎ ቁጥሮችን እንደ ጽሁፍ ማቅረብ ይችላሉ በ LibreOffice ሰንጠረዥ ውስጥ: የ ክፍል አገባብ ዝርዝር ይክፈቱ ወይንም የ ክፍሎች መጠን እና ይምረጡ የ ክፍሎች አቀራረብ - ቁጥሮች እና ከዛ ይምረጡ "ጽሁፍ" ከ ምድብ ዝርዝር ውስጥ: ማንኛውም ቁጥር የሚገባ በዚህ አቀራረብ መጠን እንደ ጽሁፍ ይተርጎማል: እነዚህ ቁጥሮች የሚታዩት እንደ "ቁጥሮች" ነው ከ ግራ-ማሰለፊያ በኩል ነው: እንደ ሌሎች ጽሁፎች

እርስዎ ቀደም ብለው መደበኛ ቁጥሮች አስገብተው ከሆነ በ ክፍሎች ውስጥ እና ከዚያ በኋላ አቀራረቡን ከ ቀየሩ የ ክፍሎቹን በ "ጽሁፍ": ቁጥሮቹ እንደ ነበሩ መደበኛ ቁጥር ሆነው ይቀራሉ: አይቀየሩም: ከዚያ በኋላ የሚገቡ ቁጥሮች ብቻ ወይንም ቁጥሮች የታረሙ የ ጽሁፍ ቁጥር ይሆናሉ

እርስዎ ቁጥር በ ቀጥታ ማስገባት ከፈለጉ እንደ ጽሁፍ: አፖስትሮፊ (') መጀመሪያ ያስገቡ: ለምሳሌ: ለ አመቶች በ አምድ ራስጌ ውስጥ: እርስዎ ማስገባት ይችላሉ '1999, '2000 እና '2001. አፖስትሮፊ በ ክፍሉ ውስጥ አይታይም: ነገር ግን የሚጠቁመው ማስገቢያው እንደ ጽሁፍ እንዲያውቅ ነው: ይህ በጣም አስፈላጊ ነው: ለምሳሌ: እርስዎ የ ስልክ ቁጥር ያስገባሉ ወይንም የ ፖስታ አድራሻ የሚጀምር በ ዜሮ (0): ምክንያቱም ዜሮ (0) በ ዲጂት ቅደም ተከተል ውስጥ ይወገዳል በ መደበኛ የ ቁጥር አቀራረብ ውስጥ

Please support us!