LibreOffice 25.2 እርዳታ
የ LibreOffice ሰንጠረዥ ትእይንት የ ክፍል ዋጋዎች ስብስብ ነው በ እርስዎ ስሌቶች ውስጥ የሚጠቀሙበት: እርስዎ ስም መመደብ ይችላሉ ለ እያንዳንዱ ትእይንት በ እርስዎ ወረቀት ውስጥ: ይግለጹ በርካታ ትእይንቶች በ ተመሳሳይ ወረቀት ውስጥ: እያንዳንዱ በ ተለየ ዋጋዎች በ ክፍሎች ውስጥ: እና ከዛ እርስዎ በ ቀላሉ መቀየር ይችላሉ የ ክፍል ዋጋዎች ስብስብ በ ስማቸው እና በፍጥነት መመልከት ይችላሉ ውጤቱን: ትእይንቶች መሳሪያዎች ናቸው ለ መሞከር "ቢሆ-ንስ" ጥያቄዎች
ትእይንት ለ መፍጠር: ይምረጡ ሁሉንም ክፍሎች ለ ትእይንት መፍጠሪያ ዳታ የሚያቀርበውን
ይምረጡ ክፍሎች ዋጋዎቹን የያዙ በ ትእይንቶች መካከል የሚቀያየሩ: በርካታ ክፍሎች ለ መምረጥ ተጭነው ይያዙ የ ትእዛዝ Ctrl ቁልፍ እያንዳንዱ ክፍል በሚጫኑ ጊዜ
ይምረጡ መሳሪያዎች - ትእይንቶች የ ትእይንቶች መፍጠሪያ ንግግር ይታያል
ለ አዲሱ ትእይንት ስም ያስገቡ እና ሌሎች ሜዳዎችን ይተዋቸው ነባር ዋጋቸው ሳይቀየር: ንግግሩን ይዝጉ በ መጫን እሺ: የ እርስዎ ትእይንት ራሱ በራሱ ይጀምራል
ትእይንቶችን በ መቃኛ ውስጥ መምረጥ ይችላሉ:
መክፈቻ መቃኛውን በ መቃኛ ምልክት በ መደበኛ እቃ መደርደሪያ ላይ
ይጫኑ የ ትእይንቶች ምልክት በ መቃኛው ላይ
በ መቃኛ ውስጥ: ለ እርስዎ ይታያል የ ተገለጸው ትእይንት ከ አስተያየት ጋር: ትእይንቱ በሚፈጠር ጊዜ የገቡ
ሁለት ጊዜ-ይጫኑ በ ትእይንት ስም ላይ በ መቃኛ ውስጥ ትእይንቱን ለ መፈጸም ወደ አሁኑ ወረቀት ውስጥ
ትእይንት ለማጥፋት: በ ቀኝ-ይጫኑ ስሙን በ መቃኛው ላይ እና ይምረጡ ማጥፊያ
ትእይንት ለማረም: በ ቀኝ-ይጫኑ ስሙን በ መቃኛው ላይ እና ይምረጡ ባህሪዎች
ድንበር ለ መደበቅ ለ ክፍሎች ማሰናጃ የ ትእይንቱ አካል ለሆኑ: ይክፈቱ የ ባህሪዎች ንግግር ለ እያንዳንዱ ትእይንት በ ክፍሎቹ ላይ ተፅእኖ ለሚፈጥረው እና ያጽዱ ዽንበር ማሳያ ምልክት ማድረጊያ ሳጥን: ድንበሩን መደበቅ እንዲሁም ያስወግዳል ዝርዝር ሳጥን በ ወረቀቱ ላይ እርስዎ ትእይንት የሚመርጡበት
እርስዎ ማወቅ ከፈለጉ የትኞቹ ዋጋዎች በ ትእይንት ውስጥ በ ሌሎች ዋጋዎች ላይ ተፅእኖ እንደሚፈጥሩ: ይምረጡ መሳሪያዎች - መርማሪ - ጥገኞችን መከታተያ ለ እርስዎ ቀስት ይታያል ወደ ክፍሎች ውስጥ በ ቀጥታ ጥገኛ የሆነውን ለ አሁኑ ክፍል