LibreOffice 25.2 እርዳታ
እርስዎ መግለጽ ይችላሉ የትኞቹ የ ክፍል መጠኖች ከ ሰንጠረዥ ላይ እንደሚታተሙ
በ ወረቀቱ ላይ የ ተገለጸው ማተሚያ መጠን ውስጥ አካል ያልሆኑ አይታተሙም ወይንም አይላኩም: ወረቀት የ ማተሚያ መጠን ውስጥ አካል ያልሆኑ አይታተሙም ወይንም አይላክም ወደ PDF ፋይል: ሰነዱ የ Excel ፋይል አቀራረብ ካልያዘ በስተቀር
በ Excel አቀራረብ የተከፈቱ ፋይሎች: ሁሉም ወረቀቶች የ ተገለጸውን ማተሚያ መጠን የያዙ ይታተማሉ: ተመሳሳይ ባህሪ ይከሰታል እርስዎ በሚልኩ ጊዜ የ Excel አቀራረብ ሰንጠረዥ ወደ PDF ፋይል
ማተም የሚፈልጉትን ክፍሎች ይምረጡ
ይምረጡ አቀራረብ - የ ማተሚያ መጠኖች - መግለጫ
ይምረጡ ክፍሎች እርስዎ መጨመር የሚፈልጉትን ወደ ነበረው የማተሚያ መጠን
ይምረጡ አቀራረብ - የ ማተሚያ መጠኖች - መጨመሪያ
ይምረጡ አቀራረብ - የ ማተሚያ መጠኖች - ማጽጃ
በ ገጽ መጨረሻ ቅድመ እይታ የ ማተሚያ መጠን እንዲሁም የ ገጽ መጨረሻ አካባቢ ይታያሉ በ ሰማያዊ ድንበር እና መሀከል ላይ የ ገጽ ቁጥር ይኖራል በ ግራጫ ቀለም: ምንም የማይታተሙ አካባቢዎች ግራጫ መደብ ይኖራቸዋል
አዲስ የ ገጽ መጨረሻ አካባቢ ለ መግለጽ: ድንበሩን ይዘው ይጎትቱ ወደ አዲሱ አካባቢ: እርስዎ ከ ገለጹ በኋላ አዲስ የ ገጽ መጨረሻ አካባቢ: ራሱ በራሱ የ ገጽ መጨረሻ ይቀየራል በ እጅ የ ገጽ መጨረሻ
ይምረጡ መመልከቻ - የ ገጽ መጨረሻ በ ቅድመ እይታ
ለ መቀየር ነባር የ ማሳያ መጠን ለ ገጽ መጨረሻ ቅድመ እይታ ሁለት ጊዜ ይጫኑ በ ፐርሰንት ዋጋ ላይ በ ሁኔታ መደርደሪያ ላይ: እና ይምረጡ አዲስ የ ማሳያ መጠን
የ ማተሚያ መጠኖች ማረሚያ
የማተሚያ መጠን ለ መቀየር: ይጎትቱ የ መጠኑን ድንበር ወደ አዲስ አካባቢ
በ እጅ በ ማተሚያ መጠን ውስጥ ያለ የ ገጽ መጨረሻ ለማጥፋት: ይጎትቱ ድንበሩን የ ገጽ መጨረሻውን ከ ማተሚያው መጠን ውጪ
የ ማተሚያ መጠን ለማጽዳት: የ ድንበሩን መጠን ይዘው ይጎትቱ ወደ ተቃራኒ አቅጣጫ ድንበር መጠን
ለ መውጣት ከ ገጽ መጨረሻ ቅድመ እይታ ይምረጡ መመልከቻ - መደበኛ