LibreOffice 24.8 እርዳታ
የ ወረቀት tab ለ አሁኑ ወረቀት ሁልጊዜ የሚታየው በ ነጭ ነው ፊት ለ ፊት ከ ሌሎች ወረቀቶች tabs. የ ሌሎቹ ወረቀት tabs ግራጫ ነው ባልተመረጠ ጊዜ: በ ሌሎች ወረቀቶች tabs ላይ በ መጫን ተጭነው ይዘው ትእዛዝCtrl እርስዎ በርካታ ወረቀት መምረጥ ይችላሉ
ይህን ይጠቀሙ Shift+ ትእዛዝ Ctrl+ገጽ ወደ ላይ ወይንም ገጽ ወደ ታች በርካታ ወረቀቶችን ለ መምረጥ የ ፊደል ገበታውን በ መጠቀም
የ ወረቀት ምርጫውን ለ መተው: ይጫኑ በ ወረቀት tab ላይ እንደገና ተጭነው ይዘው የ ትእዛዝCtrl ቁልፍ: አሁን የሚታየው ወረቀት አይወገድም ከ ምርጫው ውስጥ
እርስዎ ወደ ወረቀቶች መጠን መምራት ይችላሉ በ መቀመሪያ ውስጥ የ መጀመሪያ ገጽ እና የ መጨረሻ ገጽ መጠን በ መወሰን: ለምሳሌ =ድምር(ወረቀት1.A1:ወረቀት3.A1) ይደምራል ሁሉንም የ A1 ክፍሎች በ ወረቀት1 በሙሉ እስከ ወረቀት3.