LibreOffice 25.2 እርዳታ
እርስዎ ክፍልፋይ ቁጥሮች በ ክፍል ውስጥ ማስገባት እና ለ ስሌቶች መጠቀም ይችላሉ:
ያስገቡ "0 1/5" በ ክፍል ውስጥ (ያለ ትምህርተ ጥቅስ) እና ይጫኑ ማስገቢያ ቁልፍ: በ ማስገቢያ መስመር ላይ በ ሰንጠረዥ ከ ላይ በኩል: ለ እርስዎ ይህ ዋጋ ይታያል 0.2, ለ ስሌቶች የሚጠቀሙበት
እርስዎ ካስገቡ “0 1/2” በራሱ አራሚ ሶስቱን ባህሪዎች 1, / እና 2 ይቀይራቸዋል በ ነጠላ ባህሪ: ½. ተመሳሳይ ይፈጸማል ለ 1/4 እና 3/4. ይህ መቀየሪያ ተገልጿል በ መሳሪያዎች - በራሱ አራሚ - በራሱ አራሚ ምርጫ - ምርጫ tab ውስጥ
እርስዎ ማየት ከ ፈለጉ በርካታ-አሀዝ ክፍልፋይ እንደ "1/10": እርስዎ መቀየር አለብዎት የ ክፍል አቀራረብ ወደ በርካታ-አሀዝ ክፍልፋይ መመልከቻ: የ ክፍል አገባብ ዝርዝር ይክፈቱ: እና ይምረጡ አቀራረብ ክፍሎች ይምረጡ "ክፍልፋይ" ከ ምድብ ሜዳ ውስጥ: እና ከዛ ይምረጡ "-1234 10/81". እርስዎ ከዛ ክፍልፋይ ማስገባት ይችላሉ እንደ 12/31 ወይንም 12/32 - ያሉ ክፍልፋዮች: ነገር ግን ክፍልፋይ ራሱ በራሱ ይቀነሳል: ለ እርስዎ የሚታየው የ መጨረሻው ምሳሌ ይህ ነው 3/8.