የ ክፍል መጠኖች ማጣሪያ

እርስዎ መጠቀም ይችላሉ በርካታ ማጣሪያዎች ለማጣራት የ ክፍል መጠኖች በ ሰንጠረዥ ውስጥ: መደበኛ ማጣሪያ የሚጠቀመው ምርጫ እርስዎ የሚወስኑትን ነውለ ማጣሪያ ዳታ: በራሱ ማጣሪያ ዳታ እንደ ተወሰነው ዋጋ ወይንም ሀረግ አይነት: የ ረቀቀ ማጣሪያ የሚጠቀመው ማጣሪያ መመዘኛ ከ ተወሰኑት ክፍሎች ውስጥ ነው

በ ክፍል መጠኖች ላይ መደበኛ ማጣሪያ ለ መፈጸም

 1. ይጫኑ የ ክፍል መጠን ውስጥ

 2. ይምረጡ ዳታ - ተጨማሪ ማጣሪያዎች - መደበኛ ማጣሪያ

 3. መደበኛ ማጣሪያ ንግግር ውስጥ: እርስዎ መጠቀም የሚፈልጉትን የ ማጣሪያ ምርጫዎች ይወስኑ

 4. ይጫኑ እሺ

  እርስዎ የ ወሰኑት የ ማጣሪያ ምርጫ ተመሳሳይ መዝገብ ይታያል

በ ክፍል መጠን ላይ በራሱ መሙያ ለመፈጸም

 1. ይጫኑ በ ክፍል መጠን ወይንም የ ዳታቤዝ መጠን ውስጥ

  የ ምክር ምልክት

  እርስዎ መፈጸም ከ ፈለጉ በርካታ በራሱ ማጣሪያዎች ለ ተመሳሳይ ወረቀት: እርስዎ መጀመሪያ የ ዳታቤዝ መጠን መግለጽ አለብዎት: እና ከዛ በራሱ ማጣሪያዎች ለ ዳታቤዝ መጠኖች መፈጸሚያ


 2. ይምረጡ ዳታ - በራሱ ማጣሪያ

  የ ቀስት ቁልፍ ይጨመራል ለ እያንዳንዱ አምድ ራስጌ በ ዳታቤዝ መጠን ውስጥ

 3. ይጫኑ የ ቀስት ቁልፍ በ አምድ ውስጥ ዋጋ የያዘውን ወይንም ሀረግ እርስዎ ማሰናዳት የሚፈልጉትን የ ማጣሪያ መመዘኛ

 4. ይምረጡ ዋጋ ወይንም ሀረግ እርስዎ መጠቀም የሚፈልጉትን እንደ ማጣሪያ መመዘኛ

  እርስዎ የመረጡት መዝገቦች ከ ማጣሪያው ጋር የሚመሳሰሉ ይታያል

ማጣሪያ ከ ክፍል መጠን ውስጥ ለማስወገድ

 1. ይጫኑ በ ተጣራው ክፍል መጠን ውስጥ

 2. ይምረጡ ዳታ - ማጣሪያ - ማጣሪያ እንደ ነበር መመለሻ

Please support us!