በ ቀኖች እና ሰአቶች ማስሊያ

በ LibreOffice ሰንጠረዥ ውስጥ እርስዎ ስሌቶች መፈጸም ይችላሉ በ አሁኑ ቀን እና ሰአት ዋጋዎች: ለምሳሌ: ለማወቅ የ እርስዎን እድሜ በ ሰከንዶች ወይንም በ ሰአት: የሚቀጥሉትን ደረጃዎች ይከተሉ:

  1. በ ሰንጠረዥ ውስጥ ያስገቡ የ እርስዎን የ ልደት ቀን በ ክፍል A1.

  2. የሚቀጥለውን መቀመሪያ ያስገቡ በ ክፍል A3: =አሁን()-A1

  3. እርስዎ ከ ተጫኑ በኋላ የ ማስገቢያ ቁልፍ ውጤቱ ለ እርስዎ ይታያል በ ቀን አቀራረብ ውስጥ: ውጤቱ በ ሁለት ቀኖች መካከል ልዩነት ማሳየት አለበት እንደ ቀኖች ቁጥር: እርስዎ ክፍል A3 እንደ ቁጥር ማቅረብ አለብዎት

  4. መጠቆሚያውን በ ክፍል A3, ውስጥ ያድርጉ በ ቀኝ-ይጫኑ የ አገባብ ዝርዝር ለ መክፈት እና ካዛ ይምረጡ የ ክፍል አቀራረብ

  5. ክፍሎች አቀራረብ ንግግር ይታያል: በ ቁጥሮች tab ውስጥ: የ "ቁጥር" ምድብ በ ቀለም ደምቆ ይታያል: የ አቀራረብ ማሰናጃ ወደ "ባጠቃላይ", የ ስሌቶች ውጤት ይፈጥራል የ ቀን ማስገቢያ የያዘ እንደ ቀን የሚታይ: ውጤቱን እንደ ቁጥር ለማሳየት: የ ቁጥር አቀራረብ ማሰናጃ ይቀይሩ ወደ "-1,234" እና ይዝጉ ንግግሩን በ እሺ ቁልፍ

  6. የ ቀኖች ቁጥር በ ዛሬ እና በ ተወሰነው ቀን መካከል ያለው ይታያል በ A3 ክፍል ውስጥ

  7. በ ተጨማሪ መቀመሪያ ሙከራ ያድርጉ: በ A4 ያስገቡ =A3*24 ሰአቶች ለማስላት: በ A5 ያስገቡ =A4*60 ለ ደቂቃዎች: እና በ A6 ያስገቡ =A5*60 ለ ሰከንዶች: ይጫኑ የ ማስገቢያ ቁልፍ ከ እያንዳንዱ መቀመሪያ በኋላ

እርስዎ ከ ተወለዱበት ቀን ጀምሮ ያለውን ሰአት ማስሊያ እና ማሳያ በ ተለያዩ መለኪያዎች: ዋጋዎቹ የሚሰሉት በትክክለኛው ወቅት ነው: እርስዎ የ መጨረሻውን መቀመሪያ እንዳስገቡ እና ሲጫኑ የ ማስገቢያን ቁልፍ: ይህ ዋጋ ራሱ በራሱ አይሻሻልም: ነገር ግን "አሁን" በ ተከታታይ ይቀየራል: ዳታ ዝርዝር ውስጥ: የ ዝርዝር እቃ በ ማስሊያ – በራሱ ማስሊያ በ መደበኛ ንቁ ነው: ነገር ግን ራሱ በራሱ ማስሊያ መፈጸም አይቻልም ለ አሁን ተግባር: ይህ ማረጋገጫ ነው ለ እርስዎ ኮምፒዩተር ብቻውን እንዳይጠመድ ወረቀቱን በ ማሻሻል ላይ

Please support us!