የ ዳታ ማስገቢያ ፎርም ለ ሰንጠዥ

የ ዳታ ማስገቢያ ፎርም መሳሪያ ነው: የ ሰንጠረዥ ዳታ በ ቀላሉ ወደ ሰንጠረዥ ውስጥ ለ ማስገቢያ: የ ዳታ ማስገቢያ ፎርም: እርስዎ ማስገባት: ማረም: እና ማጥፋት ይችላሉ መዝገቦች (ወይንም ረድፎች) ዳታ እና ማስወገድ ይችላሉ የ አግድም መሸብለያ: ሰንጠረዡ በርካታ አምዶች ሲኖሩት: ወይንም አንዳንድ አምዶች በጣም ሰፊ ሲሆኑ

ይህን ትእዛዝ ለ መፈጸም...

ይምረጡ የ ዳታ - ፎርም...


በ ማሰናዳት ላይ የ ዳታ ማስገቢያ ፎርም

ውጤታማ ለ መሆን: የ ሰንጠረዥ ዳታ ሰንጠረዥ የ ራስጌ ረድፍ ሊኖረው ይገባል: የ እያንዳንዱ ክፍል ይዞታዎች የ አምድ ምልክት ነው: የ ራስጌ ክፍሎች ይዞታዎች ምልክት ይሆናሉ ለ እያንዳንዱ ዳታ ሜዳ በ ፎርሙ ውስጥ

ፎርም ማስጀመሪያ

  1. መጠቆሚያውን በ ራስጌ ረድፍ ሰንጠረዥ ላይ ያድርጉ

  2. ይምረጡ የ ዳታ - ፎርም...

ፎርሙን ዳታ በ መሙላት ላይ

በ ጽሁፍ ሜዳዎች ውስጥ ዳታ ያስገቡ: ይጫኑ ማስገቢያውን ወይንም ይጫኑ አዲስ ወደ ሰንጠረዥ ውስጥ ለ መጨመር:

የ ፎርም ንግግር ቁልፎች

አዲስ : መዝገብ መሙያ (የ ሰንጠረዥ ረድፍ ክፍሎች) በ ፎርም ሜዳ ይዞታዎች እና ይዘላል ወደ የሚቀጥለው መዝገብ ወይንም አዲስ መዝገብ ይጨምራል ከ ሰንጠረዡ በ ታች በኩል

ማጥፊያ : የ አሁኑን መዝገብ ማጥፊያ

እንደ ነበር መመለሻ: የ ፎርም ሜዳ በሚታረም ጊዜ: የ መዝገብ ሁኔታዎችን እንደ ነበር መመለሻ ወደ መጀመሪያው ሁኔታ

ያለፈው መዝገብ : ያለፈውን መዝገብ ማንቀሳቀሻ (ሰንጠረዥ ረድፍ)

የሚቀጥለው መዝገብ : ወደ የሚቀጥለው መዝገብ ማንቀሳቀሻ

መዝጊያ : ፎርም መዝጊያ

የ ፎርም ንግግር ሳጥን እና የ ራስጌ ረድፍ ክፍሎች እንደ ሜዳ ምልክቶች

የ ምክር ምልክት

ይጠቀሙ የ Tab እና Shift-Tab ቁልፎች ለ መዝለል ከ አንዱ ወደ ሌላው በ ጽሁፍ ሳጥኖች በ ፎርም ንግግር ውስጥ:


የ ምክር ምልክት

እርስዎ እንዲሁም መጠቀም ይችላሉ የ ፎርም መሸብለያ መደርደሪያ ለ መንቀሳቀስ በ ጽሁፍ ሳጥኖች መካከል


የ ፎርም ንግግር እንደገና መክፈቻ

የ ፎርም ንግግር ለ መክፈት: መጠቆሚያውን በ በ ራስጌ ረድፍ ላይ ያድርጉ እና ይክፈቱ ፎርም: የሚታየው መዝገብ በ ፎርም ንግግር የ መጀመሪያው ዳታ መዝገብ ነው: ወደ መጨረሻው መዝገብ ይውረዱ አዲስ ዳታ ከ ማስገባትዎ በፊት: ያለ በለዚያ የ አሁኑ መዝገብ ይታረማል

Please support us!