የ QB ቀለም ተግባሮች

ይመልሳል የ ቀአሰ ቀለም ኮድ የ ቀለም ኮድ ያለፈውን እንደ ቀለም ዋጋ በ አሮጌው MS-DOS የ ፕሮግራም ስርአት መሰረት

አገባብ:

የ ቀለም ኮድ (የ ቀለም ቁጥር እንደ ኢንቲጀር)

ዋጋ ይመልሳል:

Long

ደንቦች:

የ ቀለም ቁጥር : ማንኛውም የ ኢንቲጀር መግለጫ የ ቀለም ዋጋ የሚወስን ያለፈውን እንደ ቀለም ዋጋ በ አሮጌው MS-DOS የ ፕሮግራም ስርአት መሰረት

የ ቀለም ቁጥር እንደሚቀጥለው ዋጋዎች መመደብ ይቻላል:

0 : ጥቁር

1 : ሰማያዊ

2 : አረንጓዴ

3 : ሲያን

4 : ቀይ

5 : ማጄንታ

6 : ቢጫ

7 : ነጭ

8 : ግራጫ

9 : ነጣ ያለ ሰማያዊ

10 : ነጣ ያለ አረንጓዴ

11 : ነጣ ያለ ሲያን

12 : ነጣ ያለ ቀይ

13 : ነጣ ያለ ማጄንታ

14 : ነጣ ያለ ቢጫ

15 : ብሩህ ነጭ

ይህን ተግባር የሚጠቀሙት ለ መቀየር ነው አሮጌ የ MS-DOS መሰረት ያደረገ የ BASIC መተግበሪያዎች የ ላይኛውን የ ቀለም ኮድ ለሚጠቀም ነው: ተግባሩ የሚመልሰው ረጅም ኢንቲጀር ዋጋ የሚያሳየው የ ተጠቀሙትን ቀለም ነው በ LibreOffice IDE. ውስጥ

የ ስህተት ኮዶች:

5 ዋጋ የሌለው የ አሰራር ጥሪ

ለምሳሌ:


Sub ExampleQBColor
Dim iColor As Integer
Dim sText As String
    iColor = 7
    sText = "RGB= " & Red(QBColor( iColor) ) & ":" & Blue(QBColor( iColor) ) & ":" & Green(QBColor( iColor) )
    MsgBox stext,0,"Color " & iColor
End Sub

Please support us!