የ መቆጣጠሪያ እና የ ንግግር ባህሪዎች

ለ ተመረጠው ንግግር ወይንም መቆጣጠሪያ ባህሪዎች መወሰኛ ይህን ትእዛዝ ለ መጠቀም እርስዎ በ ንድፍ ዘዴ ውስጥ መሆን አለብዎት

በ ባህሪዎች ንግግር ዳታ ማስገቢያ

የሚቀጥለው የ ቁልፍ ጥምረት የሚፈጸመው ዳታ በ በርካታ መስመር ሜዳዎች ውስጥ ወይንም በ መቀላቀያ ሳጥኖች ውስጥ ለ ማስገባት ነው በ ባህሪዎች ንግግር ውስጥ:

ቁልፎች

ተጽዕኖው

Alt+ቀስት ወደ ታች

የ መቀላቀያ ሳጥን መክፈቻ

Alt+ ቀስት ወደ ላይ

የ መቀላቀያ ሳጥን መዝጊያ

Shift+ማስገቢያ

የ መስመር መጨረሻ በ በርካታ መስመር ሜዎች ላይ ማስገቢያ

(ቀስት ወደ ላይ)

ቀደም ወዳለው መስመር ይሄዳል

(ቀስት ወደ ታች)

ወደሚቀጥለው መስመር ይሄዳል

ማስገቢያ

በ ሜዳ ውስጥ ማስገቢያውን ይፈጽማል: እና መጠቆሚያው ወደሚቀጥለው ሜዳ ይሄዳል


ባጠቃላይ

ለ ተመረጠው መቆጣጠሪያ ወይንም ንግግር ባህሪዎች ይግለጽ: ዝግጁ ባህሪዎች እርስዎ እንደሚመርጡት መቆጣጠሪያ አይነት ይለያያል: ስለዚህ የሚቀጥሉት ባህሪዎች ዝግጁ አይሆኑም ለ ሁሉም አይነት መቆጣጠሪያ

ሁኔታዎች

ለ ተመረጠው ንግግር ወይንም መቆጣጠሪያ የ ሁኔታ ስራ መግለጫ: ዝግጁ ሁኔታዎች እርስዎ እንደመረጡት የ መቆጣጠሪያ አይነት ይለያያል

Please support us!