ጭረት
በ ነባር: LibreOffice ቃላቶችን ማንቀሳቀሻ በ መስመሩ ልክ የማይሆኑትን ወደሚቀጥለው መስመር: እርስዎ ከፈለጉ: ራሱ በራሱ ወይንም በ እጅ ጭረት ማድረግ ይችላሉ ይህን ባህሪ ለማስወገድ:
ራሱ በራሱ ጭረት
ራሱ በራሱ ጭረት በሚያስፈልግበት ቦታ ጭረት ያስገባል በ አንቀጽ ውስጥ: ይህ ምርጫ ዝግጁ የሚሆነው ለ አንቀጽ ዘዴዎች እና ለ እያንዳንዱ አንቀጽ ነው
ራሱ በራሱ ጭረት ለማስገባት በ ጽሁፍ አንቀጽ ውስጥ
-
በ ቀኝ-ይጫኑ በ አንቀጽ ላይ እና ይምረጡ አንቀጽ.
-
ይጫኑ የ ጽሁፍ ፍሰት tab.
-
በ ጭረት ቦታ ውስጥ: ይምረጡ ራሱ በራሱ ምልክት ማድረጊያ ሳጥን ውስጥ
-
ይጫኑ እሺ
ራሱ በራሱ ጭረት ለማድረግ በ በርካታ አንቀጾች ጽሁፍ ውስጥ
እርስዎ ከፈለጉ ራሱ በራሱ ጭረት እንዲያደርግ በ በርካታ አንቀጾች ጽሁፍ ውስጥ: የ አንቀጽ ዘዴ ይጠቀሙ
ለምሳሌ: ያስችሉ ራሱ በራሱ ጭረት ማድረጊያ ምርጫ ለ "ነባር" አንቀጽ ዘዴ: እና ከዛ ዘዴዎች ወደ አንቀጽ መፈጸሚያ እርስዎ ጭረት እንዲገባ በሚፈልጉበት
-
ይምረጡ መመልከቻ - ዘዴዎች እና ከዛ ይጫኑ የ አንቀጽ ዘዴዎች ምልክት
-
በ ቀኝ-ይጫኑ የ አንቀጽ ዘዴ በ ጭረት ለማያያዝ የሚፈልጉትን እና ከዛ ይምረጡ ማሻሻያ
-
ይጫኑ የ ጽሁፍ ፍሰት tab.
-
በ ጭረት ቦታ: ይምረጡ የ ራሱ በራሱ ምልክት ማድረጊያ ሳጥን
-
ይጫኑ እሺ
-
ለ አንቀጹ ዘዴውን መፈጸሚያ ጭረት ማድረግ የሚፈልጉትን
በ እጅ ጭረት
እርስዎ ጭረት መጨመር ይችላሉ በ መስመር ላይ በሚፈልጉበት ቦታ: ወይንም LibreOffice ጭረት የሚደርግባቸውን ቃላቶች መፈለግ እና ከዛ ጭረት የሚደረግባቸውን ማሳሰብ ይችላሉ
በ እጅ ጭረት ማድረጊያ ነጠላ ቃሎች
በፍጥነት ጭረት ለማስገባት: ይጫኑ በ ቃሉ ላይ እርስዎ ጭረት ማድረግ በሚፈልጉበት ላይ: እና ከዛ ይጫኑ ትእዛዝCtrl+ጭረት(-).
እርስዎ በ እጅ ጭረት ለ ቃላት ካስገቡ: ቃሉ ጭረት የሚደረግበት በ እጅ ብቻ ነው: ሌላ ተጨማሪ ምንም ራሱ በራሱ ጭረት አያደረግበትም ለዚህ ቃል: በ እጅ ጭረት ለ ቃላት ካስገቡ ቃሉ ጭረት ይደረግበታል ማሰናጃን ሳይጠቀሙ: በ ጽሁፍ ፍሰት tab ገጽ ውስጥ
በ እጅ ጭረት ማድረግ የሚፈልጉትን ጽሁፍ ይምረጡ
-
ጭረት ማድረግ የሚፈልጉትን ጽሁፍ ይምረጡ
-
ይምረጡ መሳሪያዎች - ቋንቋ - ጭረት