የ መስመር መጨረሻዎችን ማስወገጃ

በራሱ ማረሚያ ገጽታ ማስወገጃ ይጠቀሙ የ መስመር መጨረሻ ለማስወገድ ከ አረፍተ ነገር ውስጥ: የማይፈለግ የ መስመር መጨረሻ የሚፈጠረው እርስዎ ጽሁፍ ከሌላ ምንጭ ውስጥ ኮፒ ሲያደርጉ ነው ወደ ጽሁፍ ሰነድ ውስጥ

የ ማስታወሻ ምልክት

ይህ በራሱ ማረሚያ ገጽታ የሚሰረው ለ ጽሁፍ አቀራረብ ለ "ነባር" አንቀጽ ብቻ ነው


  1. ይምረጡ መሳሪያዎች - በራሱ ማረሚያ - በራሱ ማረሚያ ምርጫዎች

  2. ምርጫ tab: እርግጠኛ ይሁኑ የ ነጠላ አንቀጾች መቀላቀያ እርዝመት እንደሚበልጥ ከ 50% መመረጡን: አነስተኛውን ፐርሰንት ለ መምረጥ ለ መስመር እርዝመት: ሁለት ጊዜ-ይጫኑ ከ ዝርዝር ምርጫ ውስጥ: እና ከዛ አዲስ ፐርሰንት ያስገቡ

  3. ይጫኑ እሺ

  4. እርስዎ ይምረጡ የ መስመር መጨረሻ የያዘውን ጽሁፍ ማስወገድ የሚፈልጉትን

  5. ዘዴዎች መፈጸሚያ ሳጥን ውስጥ የ አቀራረብ መደርደሪያ ውስጥ ይምረጡ “ነባር”

  6. ይምረጡ መሳሪያዎች - በራሱ አራሚ - መፈጸሚያ

Please support us!