መስቀልኛ-ማመሳከሪያዎች ማስገቢያ

መስቀልኛ-ማመሳከሪያ እርስዎን የሚያስችለው በ ተወሰነ ጽሁፍ እና እቃዎች መካከል መዝለል ነው በ ነጠላ ሰነድ ውስጥ: የ መስቀልኛ-ማመሳከሪያ የያዘው ኢላማ እና ማመሳከሪያ ማስገቢያ ነው እንደ ሜዳዎች አይነት በ ሰነድ ውስጥ

እቃዎች ከ መግለጫ ጋር እና ምልክት የተደረገባቸውን እንደ ኢላማ ሊጠቀሙ ይችላሉ

ጽሁፍ መስቀልኛ-ማመሳከሪያ

መስቀልኛ-ማመሳከሪያ መጀመሪያ ከ ማስገባትዎት በፊት: በ እርስዎ ጽሁፍ ውስጥ መጀመሪያ ኢላማውን መወሰን አለብዎት

ኢላማውን ለማስገባት

  1. እንደ ኢላማ መጠቀም የሚፈልጉትን ጽሁፍ ይምረጡ ለ መስቀልኛ-ማመሳከሪያ

  2. ይምረጡ ማስገቢያ - መስቀልኛ-ማመሳከሪያ

  3. አይነት ዝርዝር ውስጥ ይምረጡ “ማመሳከሪያ ማሰናጃ”

  4. ለ ኢላማው ስም ይጻፉ በ ስም ሳጥን ውስጥ: የተመረጠው ጽሁፍ ይታያል በ ዋጋ ሳጥን ውስጥ

  5. ይጫኑ ማስገቢያ የ ኢላማው ስም ተጨምሯል ወደ ምርጫዎች ዝርዝር

ንግግሩን እንደ ተከፈት ይተዉት እና ወደሚቀጥለው ክፍል ይቀጥሉ

የ መስቀልኛ-ማመሳከሪያ ለ ኢላማው ለመፍጠር

  1. የ አይጥ መጠቆሚያውን በ ጽሁፍ ሰነዱ ውስጥ ያድርጉ መስቀልኛ-ማመሳከሪያ መጨመር በሚፈልጉበት ቦታ

  2. ይምረጡ ማስገቢያ - መስቀልኛ-ማመሳከሪያ ንግግሩን ለ መክፈት እስከ አሁን ድረስ ክፍት ካልሆነ

  3. አይነት ዝርዝር ውስጥ ይምረጡ "ማስገቢያ ማመሳከሪያ"

  4. ምርጫዎች ዝርዝር ውስጥ ኢላማውን ይምረጡ መስቀልኛ-ማመሳከር የሚፈልጉትን

  5. ማስገቢያ ማመሳከሪያዎች ወደ ዝርዝር ውስጥ ይምረጡ አቀራረብ ለ መስቀልኛ-ማመሳከሪያ አቀራረብ የሚታየውን የ መረጃውን አይነት ይወስናል እንደ መስቀልኛ-ማመሳከሪያ ለምሳሌ: "ማመሳከሪያ" የ ኢላማውን ጽሁፍ ያስገባል እና "ገጽ" የ ገጽ ቁጥር ያስገባል ወደ ታለመለት ኢላማ: ለ ግርጌ ማስታወሻ የ ግርጌ ማስታወሻ ቁጥር ይገባል

  6. ይጫኑ ማስገቢያ

  7. ይጫኑ መዝጊያ በሚጨርስ ጊዜ

መስቀልኛ-ማመሳከሪያ እቃዎችን

እርስዎ መስቀልኛ-ማመሳከር ይችላሉ በርካታ እቃዎችን በ እርስዎ ሰነድ ውስጥ: እንደ ንድፍ: መሳያ እቃዎች: የ OLE እቃዎች እና ሰንጠረዦች የመሳሰሉ: መግለጫ እስካላቸው ድረስ: ለ እቃ መግለጫ ለ መጨመር: እቃውን ይምረጡ: እና ከዛ ይምረጡ መግለጫ- ማስገቢያ

  1. ሰነዱ ውስጥ ይጫኑ መስቀልኛ-ማመሳከሪያ መጨመር በሚፈልጉበት ቦታ

  2. ይምረጡ ማስገቢያ - መስቀልኛ-ማመሳከሪያ

  3. አይነት ዝርዝር ውስጥ ይምረጡ የ እቃውን የ መግለጫ ምድብ

  4. ምርጫ ዝርዝር ውስጥ የ እቃውን መግለጫ ቁጥር ይምረጡ መስቀልኛ-ማመሳከር የሚፈልጉትን

  5. ማስገቢያ ማመሳከሪያዎች ወደ ዝርዝር ውስጥ ይምረጡ አቀራረብ ለ መስቀልኛ-ማመሳከሪያ ለ አቀራረብ የሚታየውን የ መረጃውን አይነት ይወስናል እንደ መስቀልኛ-ማመሳከሪያ ለምሳሌ "ማመሳከሪያ" የ መግለጫ ምድብ እና የ መግለጫ ጽሁፍ ወደ እቃው ያስገባል

  6. ይጫኑ ማስገቢያ

  7. ይጫኑ መዝጊያ በሚጨርስ ጊዜ

መስቀልኛ-ማመሳከሪያ ማሻሻያ

በ እጅ ለማሻሻል የ መስቀልኛ-ማመሳከሪያ በ ሰነዱ ውስጥ: ይምረጡ መሳሪያዎች - ማሻሻያ - ሜዳዎች ከ ዝርዝር ውስጥ ወይንም ይጫኑ F9.

የ ምክር ምልክት

ይምረጡ መመልከቻ - የ ሜዳ ስሞች ለ መቀያየር ከ መመልከቻው ማመሳከሪያ ስሞች እና የሚመሳከሩት ይዞታዎች መካከል


መስቀልኛ-ማመሳከሪያ ማሻሻያ

በ መቃኛ Hyperlinks ማስገቢያ

Hyperlinks ማስገቢያ

Please support us!