ስለ ራስጌዎች እና ግርጌዎች
ራስጌዎች እና ግርጌዎች ከ ላይ እና ከ ታች በኩል ያሉ ቦታዎች ናቸው በ ገጽ መስመር ውስጥ: እርስዎ ጽሁፍ ወይንም ንድፎች የሚጨምሩበት: ራስጌዎች እና ግርጌዎች ተጨምረዋል ወደ አሁኑ የ ገጽ ዘዴ ውስጥ: ማንኛውም ገጽ ተመሳሳይ ዘዴ የሚጠቀም ራሱ በራሱ ይቀበላል እርስዎ የሚጨምሩትን ራስጌ ወይንም ግርጌ: እርስዎ ማስገባት ይችላሉ ሜዳዎችእንደ የ ገጽ ቁጥሮች እና የ ምእራፍ ራስጌዎች በ ራስጌ እና ግርጌ በ ጽሁፍ ሰነድ ውስጥ
የ ገጽ ዘዴ ለ አሁኑ ገጽ ይታያል በ ሁኔታዎች መደርደሪያ ላይ.
-
ወደ ገጹ ራስጌ ለ መጨመር ይምረጡ ማስገቢያ - ራስጌ እና ግርጌ - ራስጌ እና ከዛ ይምረጡ የ ገጽ ዘዴ ለ አሁኑ ገጽ ከ ንዑስ ዝርዝር ውስጥ
-
ወደ ገጹ ግርጌ ለ መጨመር ይምረጡ ማስገቢያ - ራስጌ እና ግርጌ - ግርጌ እና ከዛ ይምረጡ የ ገጽ ዘዴ ለ አሁኑ ገጽ ከ ንዑስ ዝርዝር ውስጥ
-
እርስዎ መምረጥ ይችላሉ
ይጫኑ ወይንም tab, እና ይምረጡ ወይንም ማጽጃ ሳጥኑ ውስጥ ምልክት ያድርጉ የተለዩ ራስጌዎች እና ግርጌዎች ለ ሙሉ እና ለ ጎዶሎ ገጾች መግለጽ ከፈለጉ
-
የ ተለያዩ ራስጌዎች እና ግርጌዎች በ እርስዎ ሰነድ ውስጥ ለ መጠቀም መጨመር አለብዎት በተለያየ የ ገጽ ዘዴ እና ከዛ ይፈጽሙ ዘዴዎቹን ለ ራስጌዎች እና ለ ግርጌዎች የት እንደሚታዩ
ራስጌዎች እና ግርጌዎች በ HTML ሰነዶች ውስጥ
የ አንዳንድ ራስጌ እና ግርጌ ምርጫ ዝግጁ ነው ለ HTML ሰነዶች: ራስጌ እና ግርጌ የ ተደገፉ አይደሉም በ HTML ሰነዶች ውስጥ: እና በምትኩ የሚላኩት እንደ የተለየ tags ነው: ስለዚህ በ መቃኛ ውስጥ ይታያሉ: ራስጌ እና ግርጌ የሚላኩት በ HTML ሰነዶች ነው: እርስዎ ካስቻሉ በ ዌብ እቅድ ዘዴ ውስጥ: እርስዎ ሰነዱን እንደገና ሲከፍቱ በ LibreOffice ራስጌ እና ግርጌ በ ትክክል ይታያሉ: እንዲሁም ማንኛውም ያስገቡት ሜዳዎች በሙሉ ይታያሉ