የ ተከታታይ ሰንጠረዥ ክፍሎች ድምር ማስሊያ

  1. ይምረጡ ሰንጠረዥ - ሰንጠረዥ ማስገቢያ እና ያስገቡ ሰንጠረዥ ባለ አንድ አምድ እና ተጨማሪ ከ አንድ በላይ ረድፍ ወደ ጽሁፍ ሰነድ ውስጥ

  2. ቁጥር ይጻፉ በ አምድ ክፍሎች ውስጥ፡ ነገር ግን የ መጨረሻውን ክፍል በ አምዱ ውስጥ ባዶ ይተውት

  3. መጠቆሚያውን በ መጨረሻው ክፍል አምድ ውስጥ ያድርጉ: እና ከዛ ይጫኑ የ ድምር ምልክት ከ ሰንጠረዥ መደርደሪያ ላይ :
    መቀመሪያ መደርደሪ ይታያል ማስገቢያ ይዞ "=ድምር"

  4. ይጫኑ ከ ተከታታይ ክፍሎች በ አንዱ ላይ እርስዎ ጠቅላላ ድምሩን በሚፈልጉበት ላይ: ይጎትቱ እስከ መጨረሻው ክፍል ድረስ: እና ከዛ ይልቀቁት:
    LibreOffice የሚፈልጉትን መቀመሪያ ያስገቡ ለማስላት ድምሩን ለማግኘት በ አሁኑ አምድ ውስጥ

  5. ይጫኑ ማስገቢያውን ወይንም ይጫኑ መፈጸሚያ በ መቀመሪያ መደርደሪያ ላይ
    የ አሁኑ አምድ ጠቅላላ ድምር ወደ ክፍሉ ይገባል

በ ማንኛውም አምድ የተለየ ቁጥር ካስገቡ: የ መጨረሻውን አምድ ክፍል ሲጫኑ ድምሩ ወዲያውኑ ይሻሻላል

በ ተመሳሳይ እርስዎ በፍጥነት ማስላት ይችላሉ የ ረድፍ ቁጥሮችን ጠቅላላ ድምር

መቀመሪያ መደርደሪያ

በ ጽሁፍ ሰነድ ውስጥ ማስሊያ

ውስብስብ መቀመሪያ ማስሊያ በ ጽሁፍ ሰነዶች ውስጥ

በ መቀመሪያ በ ማስላት ላይ እና በ መለጠፍ ላይ በ ጽሁፍ ሰነድ ላይ

በ ሰንጠረዥ ባሻገር ማስሊያ

Please support us!