የ መደብ ቀለም ወይንም የ መደብ ንድፎች መግለጫ

የ መደብ ቀለም መግለጽ ይችላሉ ወይንም ለተለያዩ እቃዎች ንድፎችን እንደ መደብ መጠቀም ይችላሉ በ LibreOffice መጻፊያ

ለ ጽሁፍ ባህሪዎች መደብ መፈጸሚያ

  1. ባህሪዎቹን ይምረጡ

  2. ይምረጡ አቀራረብ - ባህሪ

  3. ይጫኑ የ መደብ tab, የ መደቡን ቀለም ይምረጡ

መደቡን ወደ አንቀጹ ላይ ለመፈጸም

  1. መጠቆሚያውን በ አንቀጹ ላይ ያድርጉ ወይንም በርካታ አንቀጾች ይምረጡ

  2. ይምረጡ አቀራረብ - አንቀጽ

  3. መደብ tab ገጽ ውስጥ ይምረጡ የ መደብ ቀለም ወይንም የ መደብ ንድፍ

የ ምክር ምልክት

ለ መደቡ እቃ ለመምረጥ ተጭነው ይያዙ ቁልፍ እና ከዛ ይጫኑ እቃውን ያለበለዚያ አማራጩን ከ መቃኛው ይጠቅሙ እቃውን ለመምረጥ


መደብ መፈጸሚያ በ ሙሉ ሰነዱ ላይ ወይንም በ ከፊል ሰነዱ ላይ

  1. መጠቆሚያውን በ ጽሁፍ ሰነድ ሰንጠረዥ ውስጥ ያድርጉ

  2. ይምረጡ ሰንጠረዥ - ባህሪዎች

  3. መደብ tab ገጽ ውስጥ ይምረጡ የ መደብ ቀለም ወይንም የ መደብ ንድፍ

  4. ሳጥን ውስጥ: ይምረጡ ቀለም ወይንም ንድፍ ለ አሁኑ ክፍል የሚፈጸመውን: ለ አሁኑ ረድፍ ወይንም ለ ጠቅላላ ሰንጠረዡ: እርስዎ በርካታ ክፍሎች ከ መረጡ ወይንም ረድፎች ንግግሩ ከ መከፈቱ በፊት: ለውጡ የሚፈጸመው ለ ተመረጠው ብቻ ነው

የ ምክር ምልክት

ምልክቶችን መጠቀም ይችላሉ መደቦችን በ ሰንጠረዥ አካል ውስጥ ለ መፈጸም


Please support us!