በ ቀጥታ መጠቆሚያ ዘዴ
ማስነሻ ወይንም ማቦዘኛ በ ቀጥታ መጠቆሚያውን እርስዎ የ ቀጥታ መጠቆሚያውን ባህሪ መግለጽ ይችላሉ በ መምረጥ LibreOffice - ምርጫዎች መሳሪያዎች - ምርጫ - LibreOffice መጻፊያ - የ አቀራረብ እርዳታ
በ ቀጥታ መጠቆሚያ የሚያስችለው እርስዎን በ ገጹ ላይ በ ባዶ ቦታዎች ጽሁፍ: ምስሎች: ሰንጠርዦች: ክፈፎች እና ሌሎች እቃዎችን ማስቀመጥ ማስቻል ነው
እርስዎ በቀጥታ መጠቆሚያውን በ ግምት በ ግራ እና በ ቀኝ መስመር ገጽ ወይንም የ ሰንጠረዥ ክፍል መሀከል ካደረጉት: እርስዎ የሚያስገቡት ጽሁፍ መሀከል ላይ ይሆናል: በቀጥታ መጠቆሚያው በ ቀኝ መስመር በኩል ከሆነ ጽሁፍ በ ቀኝ በኩል ይሰለፋል
የ በራሱ አራሚ መሳሪያዎች ራሱ በራሱ ያስወግዳል ባዶ አንቀጾች: tabs: እና ክፍተቶች በ ቀጥታ መጠቆሚያ የ ገቡ: እርስዎ በ ቀጥታ መጠቆሚያ መጠቀም ከ ፈለጉ: እርስዎ ማሰናከል አለብዎት በራሱ አራሚ መሳሪያዎችን
በ ቀጥታ መጠቆሚያ ማሰናጃ tabs መጠቆሚያውን ቦታ ማስያዣ ነው: እርስዎ tabs ከ ቀየሩ በኋላ: የ ጽሁፉ ቦታ በ ገጽ ላይ እንዲሁም ይቀየራል