ማተሚያ

ለ ፖስታ ማተሚያ ምርጫ ማሰናጃ

ይህን ትእዛዝ ለ መፈጸም...

ይምረጡ ማስገቢያ - የ ፖስታ - ማተሚያ tab


ከ እርስዎ ማተሚያ ጋር የመጣውን መምሪያ ይመልከቱ: ፖስታዎችን ለማተም እንዴት እንደሚያሰናዱ: ፖስታዎቹ በ ግራ ወይንም በ ቀኝ በኩል ወይንም መሀከል እና ፊት ወደ ላይ ወይንም ፊት ወደ ታች መሆኑን እንደ ማተሚያው አይነት ይለያያል

አግድም በ ግራ

ፖስታውን በ አግድም ማቀበያ ከ ማተሚያ ትሪ በ ግራ ጠርዝ በኩል

አግድም መሀከል

ፖስታውን በ አግድም ማቀበያ ከ ማተሚያ ትሪ መሀከል በኩል

አግድም በ ቀኝ

ፖስታውን በ አግድም ማቀበያ ከ ማተሚያ ትሪ በ ቀኝ ጠርዝ በኩል

በ ግራ በ ቁመት

ፖስታውን በ ቁመት ማቀበያ ከ ማተሚያ ትሪ በ ግራ ጠርዝ በኩል

በ ቁመት መሀከል ላይ

ፖስታውን በ ቁመት ማቀበያ ከ ማተሚያ ትሪ መሀከል በኩል.

በ ቁመት በ ቀኝ በኩል

ፖስታውን በ ቁመት ማቀበያ ከ ማተሚያ ትሪ በ ቀኝ ጠርዝ በኩል

ማተሚያ ከ ላይ

በ ማተሚያው ትሪ ውስጥ ፖስታው የሚታተምበትን ፊት ወደ ላይ በማድረግ ለ ማተሚያው ማቅረቢያ

ከ ታች ማተሚያ

በ ማተሚያው ትሪ ውስጥ ፖስታው የሚታተምበትን ፊት ወደ ታች በማድረግ ለ ማተሚያው ማቅረቢያ.

ወደ ቀኝ መቀየሪያ

በ ምን ያህል መጠን ወደ ቀኝ ከ ማተሚያው ቦታ እንደሚቀየር ያስገቡ

ወደ ታች መቀየሪያ

በ ምን ያህል መጠን ወደ ታች ከ ማተሚያው ቦታ እንደሚቀየር ያስገቡ.

የ አሁኑ ማተሚያ

የ አሁኑን ማተሚያ ስም ማሳያ

ማሰናጃ

የ ማተሚያ ማሰናጃ ንግግር መክፈቻ: እርስዎ ተጨማሪ የ ማተሚያ ማሰናጃ የሚያስተካክሉበት: እንደ ወረቀት አቀራረብ እና አቅጣጫ የሚገልጹበት

Please support us!