ባህሪዎች
እርስዎ መምረጥ ይችላሉ ከ ተለያዩ መለያዎች መካከል በ LibreOffice ሂሳብ መቀመሪያ ውስጥ: አንዳንድ መለያዎች ይታያሉ ከ ታችኛው የ አካላቶች ክፍል ውስጥ: የ እነዚህ መለያዎች ዝርዝር ይታያል በ አገባብ ዝርዝር ውስጥ በ ትእዛዞች መስኮት ውስጥ: ሁሉም መለያዎች በ አካላቶች ክፍል ውስጥ የሌሉ ወይንም በ አገባብ ዝርዝር ውስጥ በ እጅ መጻፍ ይቻላል በ ትእዛዞች መስኮት ውስጥ:
የሚቀጥሉት ሙሉ ዝርዝር ናቸው ለ ሁሉም ዝግጁ መለያዎች ለ LibreOffice ሂሳብ: ይህ ምልክት አጠገብ ያለው የ መለያ የሚያመለክተው የ አካላቶች ክፍል ውስጥ (ይምረጡ መመልከቻ - አካላቶች ) ወይንም በ አገባብ ዝርዝር ውስጥ በ ትእዛዞች መስኮት ውስጥ
በሚቀጥለው መለያ ተግባሮች ውስጥ: ይህ ፊደል "a" በ ምልክት ውስጥ የሚገልጸው ቦታ ያዢዎችን ነው: እርስዎ መመደብ የሚፈልጉትን መለያ እንደ ቅደም ተከተሉ: እርስዎ ይህን ባህሪ መቀየር ይችላሉ በ ሌላ ማንኛውም ባህሪ እርስዎ በሚመርጡት:
ተግባሮች መለያ
የ ተገለበጠ ሰርከምፍሌክስ
ማስገቢያ ከ ቦታ ያዢ ጋር በ የ ተገለበጠ ሰርከምፍሌክስ ("ምልክት ማድረጊያ") በላዩ ላይ እንዲሁም መጻፍ ይችላሉ ምልክት ማድረጊያ <?> በ ትእዛዝ መስኮት ውስጥ
መስመር ከ ላይ
ማስገቢያ ከ ቦታ ያዢ በላዩ ላይ እንዲሁም መጻፍ ይችላሉ ከ ላዩ ላይ ማስመሪያ <?> በ ትእዛዝ መስኮት ውስጥ: መስመሩ እራሱን እና እርዝመቱን ያስተካክላል
መስመር በሙሉ (መሰረዣ)
ማስገቢያ ከ ቦታ ያዢ ጋር መስመር (ወይንም በላዩ ላይ) መሰረዣ. እንዲሁም መጻፍ ይችላሉ በ ላዩ ላይ መሰረዣ <?> በ ትእዛዝ መስኮት ውስጥ
ግልጽ
ማስገቢያ ቦታ ያዢ ለ ግልጽ ባህሪ: ይህ ባህሪ ቦታ ይወስዳል "a" ነገር ግን አያሳየውም እርስዎ እንዲሁም መጻፍ ይችላሉ ፋንቶም <?> በ ትእዛዝ መስኮት ውስጥ
እንደገና መመጠኛ
የ ፊደል መጠን ለማሻሻል ትእዛዝ ማስገቢያ ከ ሁለት ቦታ ያዢ ጋር የ መጀመሪያው ቦታ ያዢ የሚያመለክተው የ ፊደል መጠን ነው: (ለምሳሌ, 12) እና ሁለተኛው ጽሁፍ ነው ለ መደበኛ አካሎች ክፍተት ያስገቡ በ ዋጋዎች መካከል: እርስዎ በቀጥታ ማስገባት ይችላሉ መጠን <?> <?> በ ትእዛዝ መስኮት ውስጥ
ፊደል መቀየሪያ
የ ፊደሉን አይነት ለ መቀየር ትእዛዝ ማስገቢያ: ከ ሁለት ቦታ ያዢ ጋር: የ መጀመሪያውን ቦታ ያዢ በ ስም ይቀይረዋል በ ፊደል ማስተካከያ : Serif, Sans ወይንም የተወሰነ ሁለተኛውን ቦታ ያዢ ይቀይረዋል በ ጽሁፍ: እርስዎ እንዲሁም መጻፍ ይችላሉ ፊደል <?> <?> በ ቀጥታ በ ትእዛዝ መስኮት ውስጥ
ይጠቀሙ የ ቀለም ትእዛዝ የ እርስዎን መቀመሪያ ቀለም ለ መቀየር: ይጻፉ ቀለም እና ከዛ ይጻፉ የ ቀለም ስም (ዝግጁ ቀለሞች እነዚህ ናቸው: ነጭ: ጥቁር: ሲያን: ማጄንታ: ቀይ: ሰማያዊ: አረንጓዴ: እና ቢጫ), ከዛ የ መቀመሪያ: ባህሪ ወይንም ተከታታይ ባህሪ: ማስገቢያ ቀለም አረንጓዴ መጠን 20 a ውጤቱ አረንጓዴ ቀለም ፊደል "a" የ ፊደል መጠን 20.
የ n ማድመቂያ እና n ማዝመሚያ ትእዛዝ ነባሩን ማድመቂያ ወይንም ማዝመሚያ ፊደሎች ያስወግዳል: ለምሳሌ: ማዝመሚያውን ያስወግዳል ከ x በ መቀመሪያ 5 x + 3=28 በ መጻፍ n ማዝመሚያ ከ x በፊት እንደ 5 n ማዝመሚያ x + 3=28.
የ መለያዎች "አኪዩት": "ባር": "ብሬቬ": "መመርመሪያ": "ክብ": "ነጥብ": "ሁለት ነጥቦች": "ሶስት ነጥቦች": "ግሬቭ": "ሀት": "ቲልዴ": እና "አቅጣጫ" የ ተወሰነ መጠኖች አላቸው: ስፋታቸውን ወይንም እርዝመታቸውን ማስተካከል አይቻልም በ ረጅም ምልክት በሚቀመጡ ጊዜ
መጠን ለ መቀየር እርስዎ መጠቀም ይችላሉ መጠን n, +n, -n, *n እና /n , የ n ቦታ ያዢ ነው: ይህ ዘዴ ጠቃሚ ነው የ ቤዝ መጠን መቀመሪያ ጉዳይ ለ መቀየር: የ ትእዛዝ መጠን +n እና መጠን -n የ ነጥብ መጠን መቀየሪያ ነው: እና መጠን *n እና መጠን /n መጠን በ ፐርሰንት መቀየሪያ ነው: ለምሳሌ የ ትእዛዝ መጠን *1.17 የ ባህሪውን መጠን ይጨምረል በ 17%.
ያስታውሱ አንዳንድ ማስገቢያዎች ክፍተት ይፈልጋሉ ለ ትክክል አካል: ይህ በ ተለይ የሚሆነው እርስዎ የ ተወሰነ ዋጋዎች በሚወስኑ ጊዜ ነው ከ ቦታ ያዢውች ይልቅ
በ በለጠ ለመረዳት ስለ አቀራረብ ከ LibreOffice ሂሳብ ውስጥ ይመልከቱ ቅንፎች እና ቡድን
መረጃ በ መለያዎች , ማውጫዎች እና ኤክስፖነንት እና መመጠኛ ሊረዳዎት ይችላል የ እርስዎን ሰነድ ለማዘጋጀት