አቋራጭ ቁልፎችን መጠቀሚያ በ LibreOffice ማስደነቂያ

የ ማስታወሻ ምልክት

አንዳንድ አቋራጭ ቁልፎች በ እርስዎ የ ዴስክቶፕ ስርአት ውስጥ ተመድበው ይሆናል: ስለዚህ በ እርስዎ የ ዴስክቶፕ ውስጥ የ ተመደቡ አቋራጭ ቁልፎች ዝግጁ አይሆኑም ለ LibreOffice. ሌላ የ ተለየ ቁልፍ ለ መመደብ ይሞክሩ: ለ LibreOffice በ መሳሪያዎች - ማስተካከያ - የ ፊደል ገበታ ወይንም በ እርስዎ የ ዴስክቶፕ ስርአት ውስጥ


እርስዎ የ ፊደል ገበታ መጠቀም ይችላሉ ለ መድረስ LibreOffice ማስደነቂያ ትእዛዞች ጋር እንዲሁም መቃኘት ይችላሉ በ ስራ ቦታ ውስጥ: LibreOffice ማስደነቂያ የሚጠቀመው ተመሳሳይ አቋራጭ ነው LibreOffice መሳያ ለ መፍጠር መሳያ እቃዎች

ቦታ ያዦችን መምረጫ

LibreOffice ማስደነቂያ በራሱ እቅድ አውጪ ቦታ ያዢ ይጠቀማል ለ ተንሸራታች አርእስት ጽሁፍ እና እቃዎች፡ ቦታ ያዢ ለመምረጥ ይጫኑ Ctrl+Enter. ወደሚቀጥለው ቦታ ያዢ ለማንቀሳቀስ፡ ይጫኑ Ctrl+Enter እንደገና

የ ማስታወሻ ምልክት

ከተጫኑ Ctrl+ማስገቢያ በ ተንሸራታቹ ውስጥ የ መጨረሻው ቦታ ያዢ ጋር ከደረሱ አዲስ ተንሸራታች ይጨመራል ከ አሁኑ ተንሸራታች ቀጥሎ፡ አዲሱ ተንሸራታች የሚጠቀመው የ አሁኑን ተንሸራታች እቅድ ነው


የ መሳያ እቃዎችን መፍጠሪያ እና ማረሚያ

  1. ይጫኑ F6 ለመቃኘት የ መሳያ መደርደሪያ

  2. ይጫኑ የ ቀኝ ቀስት ቁልፍ እቃ መደርደሪያው የ መሳያ እቃ ምልክት ጋር አስኪደርሱ ድረስ

  3. ከ ምልክቱ አጠገብ ቀስት ካለ የ መሳያ መሳሪያው ንዑስ እቃ መደርደሪያ ይከፍታል ይጫኑ ወደ ላይ ወይንም ወደ ታች ቀስት ቁልፍ ለ መክፈት የ ንዑስ እቃ መደርደሪያ: ከዛ ይጫኑ የ ቀኝ ወይንም ግራ ቁልፍ ምልክት ለ መምረጥ

  4. ይጫኑ +Enter.

    እቃው የሚፈጠረው በ አሁኑ ሰነድ መሀከል ነው

  5. ወደ ሰነድ ለ መመለስ: ይጫኑ +F6.

    እርስዎ የ ቀስት ቁልፎችን በ መጠቀም እቃዎችን በሚፈልጉት ቦታ ማድረግ ይችላሉ: ለ እቃዎች ትእዛዝ ለ መምረጥ ከ አገባብ ዝርዝር ውስጥ: ይጫኑ Shift+F10.

እቃ ለመምረጥ

  1. ይጫኑ +F6 ወደ ሰነድ ውስጥ ለ መግባት

  2. ይጫኑ Tab መምረጥ የሚፈልጉትን እቃ እስከሚያገኙ ድረስ

ተንሸራታች በሚታይበት ጊዜ

ተንሸራታች ማሳያውን ለማስጀመር ይጫኑ Ctrl+F2 ወይንምF5.

ለ መቀጠል ወደ ሚቀጥለው ተንሸራታች ወይንም ወደ ጽሁፍ እንቅስቃሴ ውጤት

የ ክፍተት መደርደሪያ

ለ መቀጠል ወደ ሚቀጥለው ተንሸራታች ምንም የ እቃ እንቅስቃሴ ውጤት ሳያጫውት

+ገጽ ወደ ታች

ቀደም ወዳለው ተንሸራታች መሄጃ

+ገጽ ወደ ላይ

ወደ ተወሰነ ተንሸራታች መሄጃ

የ ተንሸራታቹን ገጽ ቁጥር ይጻፉ እና ከዛ ይጫኑ ማስገቢያ

ተንሸራታች ማሳያ ማስቆሚያ

መዝለያ ወይንም -.

ተንሸራታች መለያ

እርስዎ መጀመሪያ የ ተንሸራታች መለያ ሲቀይሩ: ይጫኑ ማስገቢያ ለ መቀየር የ ፊደል ገበታ ትኩረት ወደ ስራ ቦታ: ያለበለዚያ ይጫኑ F6 ለ መቃኘት የ ስራ ቦታ: እና ከዛ ይጫኑ ማስገቢያ

ተንሸራታቾች መምረጥ እና አለመምረጥ

የ ቀስት ቁልፎችን ይጠቀሙ የሚፈልጉትን ተንሸራታች ለመርረጥ እና ከዛ ይጫኑ የ ክፍተት መደርደሪያ : ምርጫውን ለ መጨመር: የ ቀስት ቁልፎችን ይጠቀሙ ለ መቃኘት ተንሸራታች(ቾች) መጨመር የሚፈልጉትን እና ከዛ ይጫኑ ክፍተት መደርደሪያ እንደገና: ተንሸራታቹን ላለመምረጥ ተንሸራታች ይቃኙ እና ከዛ ይጫኑ ክፍተት መደርደሪያ :

ተንሸራታች ኮፒ በማድረግ ላይ:

  1. የ ቀስት ቁልፎችን ይጠቀሙ ኮፒ ለ ማድረግ የሚፈልጉትን ተንሸራታች ለ መቃኛ እና ከዛ ይጫኑ Ctrl+C

  2. ኮፒ የተደረገውን ተንሸራታች መለጠፍ ወደሚፈልጉበት ቦታ ያንቀሳቅሱ እና ከዛ ይጫኑ Ctrl+V.

ተንሸራታች ማንቀሳቀሻ:

  1. የ ቀስት ቁልፎችን ይጠቀሙ ማንቀሳቀስ የሚፈልጉትን ተንሸራታች ለ መቃኛ እና ከዛ ይጫኑ Ctrl+X

  2. የ ቀስት ቁልፎችን ይጠቀሙ ማንቀሳቀስ የሚፈልጉትን ተንሸራታች ለ መቃኛ እና ከዛ ይጫኑ Ctrl+V

  3. ይምረጡ በፊት ወይንም በኋላ የ አሁኑን ተንሸራታች እና ከዛ ይጫኑ እሺ

Please support us!