የ ተመጠነው ጊዜ
ለ አሁኑ ውጤት ሰአት መወሰኛ በ ውጤት ምርጫ ንግግር ውስጥ
መጀመሪያ
የተመረጠውን እንቅስቃሴ ውጤት ባህሪ ማስጀመሪያ ማሳያ የሚቀጥለው ባህሪ ማስጀመሪያ ዝግጁ ነው:
-
በሚጫኑ ጊዜ - እንቅስቃሴው ውጤቱን ያስቆማል እንደገና በ አይጥ እስከሚጫኑ ድረሰ
-
ቀደም ያለው - እንቅስቃሴው ወዲያውኑ ይጫወታል
-
ቀደም ያለው በኋላ - እንቅስቃሴው ወዲያውኑ ቀደም ያለው እንቅስቃሴ እንደጨረሰ ይጫወታል
ማዘግያ
ውጤቱ እስከሚጀምር ድረስ ተጨማሪ ማዘግያ በ ሰከንዶች መወሰኛ
የሚፈጀው ጊዜ
ውጤቱ የሚቆይበትን ጊዜ መወሰኛ
መድገሚያ
የ አሁኑ ውጤት ይደገም እንደሆን ወይንም እንዴት እንደሚደገም ይወስኑ ስንት ጊዜ እንደሚደገም ቁጥር ያስገቡ ወይንም ከ ዝርዝር ውስጥ ይምረጡ:
-
(ምንም) - ውጥጤቱ አልተደገመም
-
የሚቀጥለውን እስከሚጫኑ ድረስ - እንቅስቃሴው ይደጋገማል በ አይጥ የሚቀጥለውን እስከሚጫኑ ድረስ
-
ተንሸራታቹ እስከሚጨርስ ድረስ - እንቅስቃሴው ይደጋገማል ተንሸራታቹ እስከሚታይ ድረስ
ተጫውቶ ሲጨረስ እንደገና ማጠንጠኛ
የ እንቅስቃሴው ቅርጽ ወደ መጀመሪያው ሁኔታ ይመለስ እንደሆን መወሰኛ: እንቅስቃሴው ከ ጨረሰ በኋላ
ማንቀሳቀሻ እንደሚጫነው መጠን ይቀጥላል
እንቅስቃሴው በ መደበኛ መጫኛ ቅደም ተከተል ይጀምር እንደሆን መወሰኛ
ስጫን ውጤቱ ይጀመር
የ ተወሰነ ቅርጽ በሚጫኑ ጊዜ እንቅስቃሴው ይጀምር እንደሆን መወሰኛ
ቅርጽ በ ስም ይምረጡ ከ ዝርዝር ሳጥን ውስጥ