መመልከቻ
መግለጫ የትኛው አካላቶች በ LibreOffice ሰንጠረዥ መስኮት ውስጥ እንደሚታይ: እርስዎ ማሳየት ወይንም መደበቅ ይችላሉ የ ማድመቂያ ዋጋዎችን በ ሰንጠረዦች ውስጥ
የ መመልከቻ እርዳታ
የትኞቹ መስመሮች እንደሚታዩ መወሰኛ
መጋጠሚያ መስመሮች
የ መጋጠሚያ መስመሮች መቼ እንደሚታዩ መወሰኛ: በ ነባር የ መጋጠሚያ መስመሮች ብቻ እንዲያሳይ ነው በ ክፍሎች ውስጥ የ መደብ ቀለም ለሌላቸው: እርስዎ መምረጥ ይችላሉ የ መጋጠሚያ መስመሮች ቀለም ለማሳየት በ ክፍሎች መደብ ውስጥ: ወይንም መደበቅ: ለ ማተሚያ ይምረጡ አቀራረብ - ገጽ - ወረቀት እና ምልክት ያድርጉ በ መጋጠሚያ ምልክት ማድረጊያ ሳጥን ውስጥ
ቀለም
የ መጋጠሚያ መስመሮች ለ አሁኑ ገጽ መወሰኛ የ መጋጠሚያ መስመሮች ቀለም ለ መመልከት በ ሰነድ ውስጥ የተቀመጠ: ይሂዱ ወደ LibreOffice - ምርጫዎች መሳሪያዎች - ምርጫ - LibreOffice – የ መተግበሪያ ቀለሞች ውስጥ ገጽታ ማስገቢያውን ይፈልጉ ሰንጠረዥ – የ መጋጠሚያ መስመሮች ቀለም ማሰናጃ ይቀይሩ ወደ "ራሱ በራሱ"
የ ገጽ መጨረሻ
የ ገጽ መጨረሻ በ ተወሰነ የ ማተሚያ ቦታ ይታይ እንደሆን መወሰኛ
የ እርዳታ መስመሮች በ ማንቀሳቀስ ላይ እንዳሉ
እርስዎ ስእሎችን: ክፈፎችን: ንድፎችን: እና ሌሎች እቃዎችን በሚያንቀሳቅሱ ጊዜ መምሪያ ይታይ እንደሆን መወሰኛ እነዚህ መምሪያዎች የሚጠቅሙት እቃዎችን ለማሰለፍ ነው
ማሳያ
ለ መመልከቻ ማሳያ የ ተለያዩ ምርጫዎች ይምረጡ
መቀመሪያ
መቀመሪያ ይታይ እንደሆን መወሰኛ በ ክፍሎች ውስጥ ከ ውጤቶች ይልቅ
የ ዜሮ ዋጋዎች
ቁጥሮች ይታዩ እንደሆን መወሰኛ ዋጋቸው የሆነ 0.
አስተያየት ጠቋሚ
መወሰኛ ትንሽ አራት ማእዘን ከ ላይ በ ቀኝ ጠርዝ በኩል በ ክፍሉ ውስጥ መጠቆሚያ አስተያየት እንዳለ: አስተያየቱ የሚታየው እርስዎ ካስቻሉ ነው ጠቃሚ ምክር በ LibreOffice - ባጠቃላይ በ ምርጫ ንግግር ሳጥን ውስጥ
አስተያየት በቋሚነት ለማሳየት: ይምረጡ የ አስተያየት ማሳያ ትእዛዝ ከ ክፍሎች አገአብ ዝርዝር ውስጥ
እርስዎ አስተያየቶች መጻፍ እና ማረም ይችላሉ በ ማስገቢያ - አስተያየት ትእዛዝ: በ ቋሚነት የሚታዩ አስተያየቶችን ማረም ይቻላል በ መጫን በ አስተያየት ሳጥን ውስጥ: ይጫኑ መቃኛ እና ከ አስተያየቶች ማስገቢያ ውስጥ እርስዎ ማየት ይችላሉ ሁሉንም አስተያየቶች በ ሰነድ ውስጥ: ሁለት ጊዜ በ መጫን የ አስተያየት መቃኛ: መጠቆሚያው አስተያየቱን ወደያዘው ተመሳሳይ ክፍል ይዘላል
ዋጋ ማድመቂያ
ምልክት ያድርጉ በ ዋጋ ማድመቂያ ሳጥን ውስጥ ለማሳየት የ ክፍል ይዞታዎች በ ተለያየ ቀለም: እንደ አይነቱ ይለያያል: የ ጽሁፍ ክፍሎች አቀራረብ በ ጥቁር ነው: መቀመሪያዎች በ አረንጓዴ ነው: የ ቁጥር ክፍሎች በ ሰማያዊ ነው: እና የሚጠበቁ ክፍሎች የሚታዩት በ ነጣ ያለ ግራጫ መደብ ነው: በ ምንም የማሳያ አቀራረብ ቢቀርብ
ይህ ትእዛዝ ንቁ በሚሆን ጊዜ: በ ሰነድ ውስጥ የ ተመደቡ ምንም ቀለሞች አይታዩም ተግባሩ እስከ አልቦዘነ ድረስ
ማስቆሚያ
የ ማስቆሚያ ምልክት እቃ በሚገባ ጊዜ ይታይ እንደሆን መወሰኛ: እንደ ንድፍ አይነት በሚመረጥ ጊዜ
ጽሁፍ መጠኑን አልፏል
ክፍሉ ጽሁፍ ከያዘ ከ ክፍሉ ስፋቱ የ በለጠ: ጽሁፉ በ ባዶ ጎረቤቱ ክፍል ውስጥ ይታያል በ ተመሳሳይ ረድፍ ውስጥ: ባዶ ጎረቤት ከሌለ: ትንሽ ሶስት ማእዘን በ ክፍሉ ድንበር ይታያል ይህ ማለት ጽሁፉ ይቀጥላል ማለት ነው
ማመሳከሪያዎችን በቀለም ማሳያ
እያንዳንዱ ማመሳከሪያ በ ቀለም በ መቀመሪያ ውስጥ መድመቁን መወሰኛ: የ ክፍል መጠን ድንበሩ ወዲያውኑ በ ቀለም ይከበባል የ ክፍሉ ማመሳከሪያ ለ ማረም ከ ተመረጠ
እቃዎች
እቃዎች ይታዩ ወይንም ይደበቁ እንደሆን መወሰኛ እስከ ሶስት የ እቃ ቡድኖች
እቃዎች/ንድፎች
እቃዎች ይታዩ ወይንም ይደበቁ እንደሆን መወሰኛ
ቻርትስ
በ እርስዎ ሰነድ ውስጥ ቻርትስ ይታይ ወይንም ይደበቅ እንደሆን መወሰኛ
የ መሳያ እቃዎች
በ እርስዎ ሰነድ ውስጥ የ መሳያ እቃዎች ይታዩ ወይንም ይደበቁ እንደሆን መወሰኛ
ማሳያ
ወረቀቶች ማስማሚያ
ምልክት ከ ተደረገበት: ሁሉም ወረቀቶች በ ተመሳሳይ መጠን ይታያሉ: ምልክት ካልተደረገ ግን እያንዳንዱ ወረቀት የ ራሱ ማሳያ መጠን ይኖረዋል
መስኮት
አንዳንድ የ እርዳታ አካላቶች ይታዩ ወይንም አይታዩ እንደሆን መወሰኛ
አምድ/ረድፍ ራስጌዎች
የ ረድፍ እና አምድ ራስጌ ይታይ እንደሆን መወሰኛ
የ አግድም መሸብለያ መደርደሪያ
በ ሰነድ መስኮት ውስጥ ከ ታች በኩል የ አግድም መሸብለያ መደርደሪያ ይታይ እንደሆን መወሰኛ
በ ቁመት መሸብለያ
በ ሰነድ መስኮት ውስጥ በ ቀኝ በኩል የ ቁመት መሸብለያ መደርደሪያ ይታይ እንደሆን መወሰኛ
የ ወረቀት tabs
የ ወረቀት tabs በ ሰንጠረዥ ከ ታች በኩል ይታይ እንደሆን መወሰኛ እዚህ ሳጥን ውስጥ ምልክት ካልተደረገ: እርስዎ መቀየር የሚችሉት በ ወረቀቶች መከከል ነው በ መቃኛ መቃኛ ውስጥ
የ ምልክቶች እቅድ
እርስዎ ከ ገለጹ የ ረቂቅ ረቂቅ የ ረቂቅ ምልክቶች ምርጫ ይታይ እንደሆን ይወስናል: የ ረቂቅ ምልክቶች በ ወረቀቱ ድንበር ላይ