የ መተግበሪያ ቀለሞች
ቀለሞች ማሰናጃ ለ LibreOffice ተጠቃሚ ገጽታ እርስዎ የ አሁኑን ማሰናጃ እንደ ገጽታ ማስቀመጫ እና በኋላ መጫን ይችላሉ
የ ቀለም ገጽታ
የ ቀለም ገጽታዎች ማስቀመጫ እና ማጥፊያ
ገጽታ
መጠቀም የሚፈልጉትን የ ገጽታ ቀለም ይምረጡ
ማስቀመጫ
የ አሁኑን ማሰናጃ እንደ ገጽታ ማስቀመጫ እና በኋላ መጫኛ ስሙ ይጨመራል ወደ ገጽታ ሳጥን ውስጥ
የ ቀለም ገጽታ ስም
ስም ያስገቡ ለ ቀለም እቅድ
ማጥፊያ
የሚታየውን የ ቀለም ገጽታ ማጥፊያ ከ ገጽታ ሳጥን ውስጥ: እርስዎ ነባር ገጽታ ማጥፋት አይችሉም
ገጽታ
ለ ተጠቃሚ ገጽታ አካሎች ቀለም ይምረጡ
በ ተጠቃሚ ገጽታ አካል ላይ ቀለም ለ መፈጸም: እርግጠኛ ይሁኑ ምልክት ማድረጊያ ሳጥን ከ ስሙ በፊት ምልክት እንደ ተደረገበት: የ ተጠቃሚ ገጽታ አካል ለ መደበቅ ምልክቱን ያጽዱ
አንዳንድ የ ተጠቃሚ ገጽታ አካላቶችን መደበቅ አይቻልም
የ መጠቆሚያ መመልከቻውን ለማሻሻል: ተጠቃሚው የ መተግበሪያ መደብ ቀለም ካሰናዳ በ 40% እና 60% ግራጫ መካከል: ራሱ በራሱ ወደ 40% ግራጫ ይቀየራል
የ ራሱ በራሱ ቀለም ማሰናጃ የ ተጠቃሚ ገጽታ አካሎችን ይቀይራል ወደ ነበረበት ቀለም ከ ቀለም ገጽታ ውስጥ
የ ቀለም ማሰናጃ ለ "ተጎበኙ አገናኞች" እና "ላልተጎበኙ አገናኞች" የሚፈጸመው ማሰናጃው ከ ተፈጸመ በኋላ ለ ተፈጠሩ ሰነዶች ብቻ ነው