መተው በ ቀጥታ አቀራረብ ለ ሰነድ

እርስዎ መተው ይችላሉ ሁሉንም አቀራረብ በ ዘዴዎች ያልተፈጸመውን በ ጥቂት ደረጃዎች

በ ቀጥታ እና የ ዘዴዎች አቀራረብ

እርስዎ ያለ ዘዴዎች ሰነድ ካቀረቡ እንደ: "በ ቀጥታ" አቀራረብ: ይህ ማለት ጽሁፍ ማሻሻል ወይንም ሌሎች እቃዎች: እንደ ክፈፎች ወይንም ሰንጠረዦች: በ ቀጥታ በ ተለያዩ መለያዎች መፈጸም ነው: አቀራረብ የሚፈጸመው ለ ተመረጠው ቦታ እና ለ ሁሉም ለውጦች ለየብቻ መፈጸም አለበት: ዘዴዎች በ ሌላ አነጋገር: በ ጽሁፍ ላይ በ ቀጥታ አይፈጸሙም: ነገር ግን ይገለጻሉ በ ዘዴዎች እና አቀራረብ መስኮት ውስጥ እና ይፈጸማሉ: አንዱ ጥቅም እርስዎ ዘዴዎችን በሚቀይሩ ጊዜ: ዘዴው የ ተፈጸመበት ሁሉም አካል በ ሰነድ ውስጥ በ ተመሳሳይ ጊዜ ይሻሻላል

ማስወገድ ይችላሉ በቀጥታ አቀራረብ ከ እርስዎ ሰነዶች ውስጥ በመምረጥ ጠቅላላ ጽሁፉን በ አቋራጭ ቁልፎች +A እና ከዛ ይምረጡ አቀራረብ - በቀጥታ አቀራረብ ማጽጃ

ማስወገጃ ሁሉንም በ ቀጥታ አቀራረብ ከ LibreOffice መጻፊያ ሰነድ ውስጥ

  1. ይጫኑ Ctrl+A ጠቅላላ ጽሁፉን ለ መምረጥ

  2. ይምረጡ አቀራረብ - በ ቀጥታ አቀራረብ ማጽጃ

ማስወገጃ ሁሉንም በ ቀጥታ አቀራረብ ከ LibreOffice ሰንጠረዥ ሰነድ ውስጥ

  1. የ Shift ቁልፍ ተጭነው ይዘው ይጫኑ የ መጀመሪያውን እና ከዛ የ መጨረሻውን ወረቀት tab ሁሉንም ወረቀቶች ለ መምረጥ

  2. ይጫኑ Ctrl+A ጠቅላላ ጽሁፉን ለ መምረጥ

  3. ይምረጡ አቀራረብ - በ ቀጥታ አቀራረብ ማጽጃ

ማስወገጃ ሁሉንም በ ቀጥታ አቀራረብ ከ LibreOffice ማቅረቢያ ሰነድ ውስጥ

  1. ይጫኑ የ ረቂቅ tab የ ረቂቅ መመልከቻ ለ መክፈት

  2. ይጫኑ Ctrl+A ጠቅላላ ጽሁፉን ለ መምረጥ

  3. ይምረጡ አቀራረብ - በ ቀጥታ አቀራረብ ማጽጃ

Please support us!