አቋራጮች (LibreOffice መድረሻ)
እርስዎ መቆጣጠር ይችላሉ LibreOffice ያለ አይጥ አካል: የ ፊደል ገበታ ብቻ በ መጠቀም
በ እያንዳንዱ ክፍሎች ዋናው የ እርዳታ ገጽ ውስጥ (ለምሳሌ: የ LibreOffice መጻፊያ ወይንም LibreOffice ሰንጠረዥ ዋናው የ እርዳታ ገጽ ውስጥ) አገናኝ አለ ለ መድረስ በ ፊደል ገበታ አቋራጮች ወደ እርዳታ ክፍል
በ ተጨማሪ በ ቁልፍ ቃል "መድረሻ" ስር: እርስዎ ያገኛሉ ደረጃ-በ-ደረጃ ትእዛዞች እንዴት እንደሚቆጣጠሩ ክፍሎችን ያለ አይጥ አካል
መስራት በ LibreOffice የ ተጠቃሚ ገጽታ ያለ አይጥ መጠቆሚያ
ዝርዝር መደርደሪያ: በ መስኮቶች እና በ ሰነድ ውስጥ ማስጀመሪያ
በ ተከታታይ መጫን F6 ትኩረቱን ይቀይራል እና በሚቀጥሉት እቃዎች ውስጥ ይዘዋወራል:
-
ዝርዝር መደርደሪያ
-
ሁሉንም የ እቃ መደርደሪያ ከ ላይ እስከ ታች እና ከ ግራ ወደ ቀኝ
-
ሁሉንም ነፃ መስኮት ከ ግራ ወደ ቀኝ
-
ሰነድ
ይጫኑ Shift+F6 በ እቃዎች ውስጥ ለ መቀያየር በ ተቃራኒ አቅጣጫ
ይጫኑ ትእዛዝCtrl+F6 በ ሰነድ ውስጥ ለ መቀየር
ይጫኑ F10 ለ መቀየር የ ዝርዝር መደርደሪያ እና ወደ ኋላ
መዝለያ ቁልፍ ይዘጋል የ ተከፈተ ንዑስ ዝርዝር: የ እቃ መደርደሪያ: ወይንም አሁን የ ተከፈተውን ነፃ መስኮት
ዝርዝር ትእዛዝ ለ መጥራት
ይጫኑ ምርጫAlt ወይንም F6 ወይንም F10 ለ መምረጥ የ መጀመሪያ ዝርዝር (የ ፋይል ዝርዝር). በ ቀኝ ቀስት: የሚቀጥለው ዝርዝር በ ቀኝ በኩል ያለው ይመረጣል: በ ግራ ቀስት ያለፈው ዝርዝር ይመረጣል
ቀስት ወደ ታች የ ተመረጠውን ዝርዝር ይከፍታል: ማንኛውም ተጨማሪ ቀስት ወደ ታች እና ቀስት ወደ ላይ በ ምርጫው ውስጥ ያንቀሳቅሳል በ ዝርዝር ትእዛዝች ውስጥ: በ ቀኝ ቀስት እርስዎ ማንኛውንም ንዑስ ዝርዝር መክፈት ይችላሉ
ይጫኑ ማስገቢያውን የ ተመረጠውን ዝርዝር ትእዛዝ ለ መፈጸም
የ ምልክት ትእዛዝ መፈጸሚያ
ይጫኑ F6 በ ተከታታይ የ መጀመሪያው ምልክት በ እቃ መደርደሪያ ላይ እስከሚመረጥ ድረስ: ይጠቀሙ የ ቀኝ ወይንም የ ግራ ቀስቶች ምልክት ለ መምረጥ በ አግድም ከ እቃ መደርደሪያ ላይ: በ ተመሳሳይ: የ ላይ ወይንም የ ታች ቀስቶች ምልክት ለ መምረጥ በ ቁመት ከ እቃ መደርደሪያ ላይ: የ ቤት ቁልፍ የሚመርጠው የ መጀመሪያውን ምልክት ነው በ እቃ መደርደሪያ ላይ እና የ መጨረሻ ቁልፍ የ መጨረሻውን ምልክት ነው
ይጫኑ ማስገቢያውን የ ተመረጠውን ምልክት ለ መፈጸም: የ ተመረጠው ምልክት በ ተከታታይ የ አይጥ ቁልፍ መጫን የሚፈልግ ከሆነ: እንደ አራት ማእዘን ማስገቢያ: እና ከዛ የ ማስገቢያ ቁልፍ መጫን ብቻ በቂ ላይሆን ይችላል: ይህ ሲያጋጥም ይጫኑ ትእዛዝ Ctrl+ማስገቢያውን
-
ይጫኑ ትእዛዝCtrl+ማስገቢያ በ ምልክት ላይ የ መሳያ እቃ ለ መፍጠር: የ መሳያ እቃ በ መመልከቻው መሀከል ላይ ይታያል: በ ቅድሚያ በ ተገለጸ መጠን
-
ይጫኑ ትእዛዝ Ctrl+ማስገቢያ በ ምርጫው እቃ ላይ የ መጀመሪያውን የ መሳያ እቃ ለ መምረጥ በ ሰነድ ውስጥ: እርስዎ ማረም ከ ፈለጉ: መጠን ወይንም ማንቀሳቀስ የ ተመረጠውን የ መሳያ እቃ: መጀመሪያ ይጠቀሙ ትእዛዝCtrl+F6 ትኩረቱን ወደ ሰነድ ውስጥ ለማሰናዳት
የ እቃ መደርደሪያው መመልከቻው ሊያሳየው ከሚችለው በላይ ከሆነ: ምልክት ያሳያል በ ቀኝ በኩል ከ ታች ጠርዝ በኩል: የ እቃ መደርደሪያውን ይምረጡ እና ይጫኑ ገጽ ወደ ላይ ወይንም ገጽ ወደ ታች ቀሪውን ምልክቶች ለማሳየት
የ ተለየ ፍንጭ ለ እቃ መደርደሪያው
ይጫኑ ቀስት ወደ ታች ወይንም የ ቀኝ ቀስት የ ተመረጠውን የ እቃ መደርደሪያ ለ መክፈት: ይህ እኩል ነው ከ አይጥ መጫኛ ጋር: በ እቃ መደርደሪያው ላይ የ ቀኝ ቀስት ይጠቀሙ እና የ ግራ ቀስት ቁልፎች: የ ቤት እና መጨረሻ ቁልፎች የ መጀመሪያ እና የ መጨረሻ ምልክት ይመርጣሉ በ እቃ መደርደሪያው ላይ በትክክል:
የ እቃ መደርደሪያውን ይዝጉ በ Esc ቁልፍ: የ እቃ መደርደሪያውን ማንቀሳቀስ ካልተቻለ ያለ አይጥ መጠቆሚያ
ከ መቀላቀያ ሳጥን ውስጥ መምረጫ
ይምረጡ መቀላቀያ ሳጥን: እና ይጫኑ ማስገቢያውን
ይጠቀሙ ቀስት ወደ ታች ወይንም ቀስት ወደ ላይ ቁልፍ ወደ ታች ለ መሸብለል በ መቀላቀያ ሳጥን ማስገቢይ ውስጥ: ወይንም ቀስት ወደ ላይ ወይንም ገጽ ወደ ላይ ወደ ላይ ለ መሸብለል: የ ቤት ቁልፍ ወደ መጀመሪያው ማስገቢያ ይወስዶታል: እና የ መጨረሻ ቁልፍ ወደ መጨረሻው ማስገቢያ ይወስዶታል:
የ ተመረጠውን ማስገቢያ ለ መፈጸም ይጫኑ ማስገቢያውን
በ ሰንጠረዥ ውስጥ መምረጫ
በ በርካታ መስኮቶች: ንግግሮች: እና የ ሰንጠረዥ መቆጣጠሪያ ሜዳ ውስጥ: እርስዎ ዳታ የሚመርጡበት ሰንጠረዦች አሉ: ለምሳሌ: የ ቀኝ ክፍል ለ ዳታ ምንጭ መመልከቻ የሚቀጥሉትን ቁልፎች ይጠቀሙ ለ መምረጫ ከ እነዚህ ሰንጠረዦች ውስጥ:
-
የ ክፍተት ማስገቢያ: ይቀይራል ከ አሁኑ የ ረድፍ ምርጫ እና ይሰርዛል ማንኛውንም ምርጫ: ነገር ግን የ አሁኑ ክፍል በ ማረሚያ ዘዴ ውስጥ ከሆነ ግን አይቻልም
-
ትእዛዝCtrl+የ ክፍተት ማስገቢያ: በ አሁኑ የ ረድፍ ምርጫ እና የ መሰረዣ ምርጫ መካከል ይቀያይራል
-
ትእዛዝCtrl+Shift+የ ክፍተት ማስገቢያ: በ አሁኑ የ አምድ ምርጫ እና የ መሰረዣ ምርጫ መካከል ይቀያይራል
-
ምርጫ Alt+ቀስት ወደ ላይ ወይንም ምርጫ Alt+ቀስት ወደ ታች: የ መስኮት መለያያ ያንቀሳቅሳል በ ፎርም እና ሰንጠረዥ መካከል: ለምሳሌ: የ ጽሁፎች ዝርዝር ዳታቤዝ ውስጥ
-
በ ሰንጠረዥ መቆጣጠሪያ ውስጥ ወይንም የ ዳታ ምንጭ መመልከቻ ውስጥ: የ Tab ቁልፍ ወደሚቀጥለው አምድ ያንቀሳቅሳል: ወደሚቀጥለው መቆጣጠሪያ ለ መንቀሳቀስ ይጫኑ ትእዛዝCtrl+Tab. ወዳለፈው መቆጣጠሪያ ለ መንቀሳቀስ ይጫኑ Shift+ትእዛዝCtrl+Tab.
የ መስኮቶች እና ንግግሮች መጠን እና ቦታ
-
መጀመሪያ ይጫኑ ምርጫ Alt+የ ክፍተት ማስገቢያ ቁልፍ
የ ስርአቱ ዝርዝር ይከፈታል ከ ዝርዝር ትእዛዞች ጋር እንደ ማንቀሳቀሻ እንደገና መመጠኛ እና መዝጊያ.
-
ትእዛዝ ይምረጡ (ቀስት ወደ ታች: ማስገቢያ)
-
እርስዎ አሁን የ ቀስት ቁልፎች መጠቀም ይችላሉ ለ ማንቀሳቀስ: ወይንም ንግግር ወይንም መስኮት እንደገና ለ መመጠን
-
ይጫኑ ማስገቢያ ለውጦቹን ለ መቀበል: ይጫኑ መዝለያውን ለውጦቹን ለ መሰረዝ
መስኮቶች እና የ እቃ መደርደሪያ ማሳረፊያ እና ማባረሪያ
-
ይጫኑ F6 መስኮት ወይንም እቃ መደርደሪያ እስከሚመረጥ ድረስ
-
ይጫኑ ትእዛዝCtrl+Shift+F10.
እቃዎችን መምረጫ
ይጫኑ Shift+F4 የ መጀመሪያውን እቃ ለ መምረጥ ከ አሁኑ ሰነድ ውስጥ: እቃው ሲመረጥ: ይጫኑ Tab የሚቀጥለውን እቃ ለ መምረጥ: ወይንም ይጫኑ Esc ወደ ጽሁፉ ለ መመለስ
እቃዎች ማረሚያ
የ ተመረጠውን የ OLE እቃ ማስጀመር ይቻላል ማስገቢያ ቁልፍ በ መጫን
የ እቃዎች መጠን እና ቦታ ማረሚያ
-
ይጠቀሙ የ ቀስት ቁልፎች ለማንቀሳቀስ የ ተመረጠውን እቃ አንድ መጋጠሚያ ሪዞሊሽን ክፍል
የ መጋጠሚያ ሪዞሊሽን ማሰናጃ እስከ በ LibreOffice - ምርጫዎችመሳሪያዎች - ምርጫ - LibreOffice መጻፊያ - መጋጠሚያ በ ሪዞሊሽን ቦታ ውስጥ: እርስዎ ቁጥር ካስገቡ ከ 1 የ በለጠ በ ንዑስ ክፍል ቦታ ውስጥ: እርስዎ የ ቀስት ቁልፍ መጫን አለብዎት ቁጥሩ እንደሚያሳየው የ ተመረጠውን እቃ ለማንቀሳቀስ በ አንድ መጋጠሚያ ሪዞሊሽን ክፍል
-
ይጠቀሙ የ ምርጫAlt እና ቀስት ቁልፎች የ ተመረጠውን እቃ በ አንድ ፒክስል ለማንቀሳቀስ
-
ይጠቀሙ ትእዛዝCtrl+Tab ወደ ማረሚያ ዘዴ እጄታ ለ መግባት: የ ላይኛው የ ግራ እጄታ ነው ንቁ እጄታ: ብልጭ ድርግም ማለት ይጀምራል: ይጠቀሙ ትእዛዝCtrl+Tab የሚቀጥለውን እጄታ ለ መምረጥ: ይጫኑ መዝለያውን ከ እጄታ ማረሚያ ዘዴ ለ መውጣት
-
በ እጄታ ማረሚያ ዘዴ ውስጥ: የ ቀስት ቁልፎች የ ተመረጠውን እጄታ ያንቀሳቅሳሉ: ስለዚህ የ እቃው መጠን ይቀየራል
የ እቃዎች ማስቆሚያ ማረሚያ
እርስዎ ማንቀሳቀስ ይችላሉ የ እቃ ማስቆሚያ በ ቀስት ቁልፎች: መጀመሪያ ወደ ማረሚያ ዘዴ እጄታ ይግቡ እና ይምረጡ ማስቆሚያ: እንደ ማስቆሚያው አይነት: እርስዎ ማስቆሚያውን ማንቀሳቀስ ይችላሉ በ ተለያየ አቅጣጫ
-
እቃ ይምረጡ
-
ወደ ማረሚያ ዘዴ እጄታ መግቢያ በ ትእዛዝCtrl+Tab.
-
የ ላይኛው የ ግራ ንቁ እጄታ: ብልጭ ድርግም ማለት ይጀምራል: ይጫኑ ትእዛዝ Ctrl+Tab በርካታ ጊዜ: እጄታ: ብልጭ ድርግም ማለት እስኪያቆም: ይህ ለ እርስዎ ምልክት ነው የ ማስቆሚያው እቃ መጀመሩን እርስዎ በ ጽሁፍ ሰነዶች ውስጥ ይጫኑ Shift+ ትእዛዝ Ctrl+A ማስቆሚያውን በ ቀጥታ ለማስጀመር
-
ማስቆሚያውን ለማንቀሳቀስ የ ቀስት ቁልፎች ይጠቀሙ: እቃው ማስቆሚያውን ይከተላል
እርስዎ የ ተመረጠውን እቃ ማስቆሚያ መቀየር ይችላሉ: ለምሳሌ: በ እቃዎች አገባብ ዝርዝር ውስጥ
-
እቃውን ካስቆሙ በ አንቀጽ ውስጥ: የ ቀስት ቁልፎች እቃውን ያንቀሳቅሳሉ ወዳለፈው ወይንም ወደሚቀጥለው የ አንቀጽ ቦታ
-
እቃውን ካስቆሙ በ ገጽ ውስጥ: ገጽ ወደ ላይ እና ገጽ ወደ ታች እቃውን ያንቀሳቅሳሉ ወዳለፈው ወይንም ወደሚቀጥለው ገጽ ውስጥ
-
እቃውን ካስቆሙ በ ባህሪ ውስጥ: የ ቀስት ቁልፎች እቃውን ያንቀሳቅሳሉ በ አንቀጽ ውስጥ
-
እቃውን ካስቆሙ በ ባህሪ ውስጥ: ምንም የ ማስቆሚያ ምልክት አይኖርም: ስለዚህ እርስዎ እቃውን ማንቀሳቀስ አይችሉም
-
እቃውን ካስቆሙ በ ክፈፍ ውስጥ: የ ቀስት ቁልፎች እቃውን ያንቀሳቅሳሉ ወደሚቀጥለው የ ክፈፍ አቅጣጫ ውስጥ
የ መከፋፈያ መስመሮች መቆጣጠሪያ
ሰነዶች የ LibreOffice ሰንጠረዥ LibreOffice መሳያ እና LibreOffice ማስደነቂያ መክፈል ይቻላል በ አግድም እና በ ቁመት ወደ ተለያየ መመልከቻዎች ውስጥ: እያንዳንዱ መመልከቻ የ ሰነዱን የ ተለያየ ክፍል ማሳየት ይችላል: የ አይጥ ቁልፍ በ መጠቀም: እርስዎ መጎተት ይችላሉ የ መከፋፈያ መስመር ከ መሸብለያ መደርደሪያ ላይ በ ሰነድ ውስጥ
-
Shift+ትእዛዝCtrl+F6: የ መከፋፈያ መስመሮች ያሳያል በ ነባር ቦታዎች ላይ እና ትኩረቱን በ መስመር ላይ ያደርጋል
-
የ ቀስት ቁልፎች: የ አሁኑን መከፋፈያ መስመር በ ትልቅ ደረጃ በ ቀስቱ አቅጣጫ ያንቀሳቅሰዋል
-
Shift+የ ቀስት ቁልፎች: የ አሁኑን መከፋፈያ መስመር በ ትንሽ ደረጃ በ ቀስቱ አቅጣጫ ያንቀሳቅሰዋል
-
ማጥፊያ: የ አሁኑን መከፋፈያ መስመር ማጥፊያ
-
Shift+ማጥፊያ: ሁለቱንም የ መከፋፈያ መስመሮች ማጥፊያ
-
ማስገቢያ: በ አሁኑን ቦታ የ መከፋፈያ መስመሮች ይጠግናል
-
መዝለያ: የ አሁኑን መከፋፈያ መስመር ወደ ነባር ቦታው እንደ ነበር መመለሻ
የ ዳታ ምንጭ መመልከቻ መቆጣጠሪያ
ትእዛዝ Ctrl + Shift + F4 መክፈቻ እና መዝጊያ የ ዳታ ምንጭ መመልከቻ
F6: በ ሰነድ እና በ እቃ መደርደሪያ መካከል መቀያየሪያ
+ (መደመሪያ ቁልፍ): የ ተመረጠውን ማስገቢያ ያሰፋል ለ ዳታ ምንጭ መቃኛ
- (መቀነሻ ቁልፍ): የ ተመረጠውን ማስገቢያ ያሳንሳል ለ ዳታ ምንች
ትእዛዝCtrl+Shift+E: ከ ዳታ ምንጭ መቃኛ እና ሰንጠረዥ ውስጥ ለ መቀያየር
አቋራጮች በ ጥያቄ ንድፍ መስኮት ውስጥ
F6: በ እቃ መደርደሪያ: በ ሰንጠረዥ መመልከቻ: እና በ ተመረጠው ቦታ መካከል መቀያየሪያ
ምርጫAlt+ቀስት ወደ ላይ ወይንም ምርጫAlt+ቀስት ወደ ታች: ያንቀሳቅሳል በ ሰንጠረዥ መመልከቻውን እና የ መምረጫ ቦታ ወደ ላይ ወይንም ወደ ታች በ ድንበር መካከል
ቁልፎች በ ሰንጠረዥ መመልከቻ ውስጥ (በ ጥያቄ ንድፍ ውስጥ ከ ላይ በኩል) እና ከ መስኮቱ ግንኙነት
ትእዛዝCtrl+የ ቀስት ቁልፍ: የ ተመረጠውን ሰንጠረዥ በ ቀስቱ አቅጣጫ ያንቀሳቅሳል
ትእዛዝCtrl+Shift+የ ቀስት ቁልፍ የ ተመረጠውን ሰንጠረዥ በ ሰንጠረዥ መመልከቻ እንደገና ይመጥናል
ማጥፊያ: የ ተመረጠውን ሰንጠረዥ ወይንም ግንኙነት ከ ሰንጠረዥ መመልከቻ ላይ ማስወገጃ
Tab: በ ሰንጠረዥ እና በ ሰንጠረዥ ግንኙነቶች መመልከቻ መካከል መቀያየሪያ
ማስገቢያ: ግንኙነት ሲመረጥ: የ ማስገቢያ ቁልፍ ይክፍታል የ ባህሪዎችንግግር ለ ግንኙነት
ማስገቢያ: ሰንጠረዥ በሚመረጥ ጊዜ: የ ማስገቢያ ቁልፍ ያስገባል የ መጀመሪያውን ዳታ ሜዳ ከ ዝርዝር ሳጥን ውስጥ ወደ ተመረጠው ቦታ
ቁልፎች በ ምርጫ ቦታ (በ ጥያቄ ንድፍ ከ ታች በኩል)
ትእዛዝCtrl+የ ግራ ቀስት ወይንም የ ቀኝ ቀስት: የ ተመረጠውን አምድ ወደ ግራ ወይንም ወደ ቀኝ ያንቀሳቅሳል
ቁልፎች በ ሰንጠረዥ ንድፍ መስኮት ውስጥ
F6: በ እቃ መደርደሪያ: በ አምድ መመልከቻ: እና በ ባህሪዎች ቦታ መካከል መቀያየሪያ
የ ምስል ካርታ ማረሚያ መቆጣጠሪያ
-
ይጫኑ Tab ምልክት ለ መምረጥ: እርስዎ አንዱን ምልክት ከ መረጡ ከ አራት ማእዘን ወደ ነፃ እጅ ፖሊጎን እና እርስዎ ከ ተጫኑ የ ትእዛዝ Ctrl+ማስገቢያ: የ ተመረጠው እቃ አይነት ይፈጠራል እንደ ነባሩ መጠን
-
እርስዎ ማስገቢያውን ከ ተጫኑ የ ምልክት ይምረጡ ሲመረጥ: ትኩረቱ ይሰናዳል ወደ ምስል መስኮት የ ምስል ካርታ አራሚ: ይጫኑ Esc ለማሰናዳት ትኩረቱን ወደ ነበረበት ወደ ምልክት እና ማስገቢያ ሳጥኖች ውስጥ
-
የ ይምረጡ ምልክት ከ ተመረጠ እና እርስዎ ከ ተጫኑ Ctrl+ማስገቢያ: የ መጀመሪያው እቃ በ ምስል መስኮት ውስጥ ይመረጣል
-
ይጠቀሙ ምልክት የ ነጥቦች ማረሚያ ለ መቀያየር ወደ ነጥቦች ማረሚያ ዘዴ ለ ፖሊጎን እና ወደ ኋላ ለመመለስ
-
ይጠቀሙ Ctrl+Tab በ ምስል መስኮት ውስጥ ለ መምረጥ የሚቀጥለውን ነጥብ: ይጠቀሙ Shift+Ctrl+Tab ያለፈውን ነጥብ ለ መምረጥ
-
የ ተመረጠውን እቃ ለ ማጥፋት ይጠቀሙ የ ማጥፊያ ቁልፍ ትኩረቱን በ ምስል መስኮት ውስጥ አድርገው
እርዳታ መቆጣጠሪያ
ይጫኑ Shift+F1 ለማሳየት የ ተስፋፉ ምክሮች አሁን ለተመረጠው ትእዛዝ: ምልክት ወይንም መቆጣጠሪያ
ዋናውን የ እርዳታ ገጾች መቃኛ
-
በ ዋናው የ እርዳታ ገጽ ውስጥ: ይጠቀሙ Tab ለ መዝለል ወደሚቀጥለው hyperlink ወይንም Shift+Tab ለ መዝለል ወዳለፈው አገናኝ
-
የ ተመረጠውን ማስገቢያ ለ መፈጸም ይጫኑ ማስገቢያውን
-
ይጫኑ የ ኋሊት ደምሳሽን ከ ማስገቢያው በላይ በኩል ያለውን ቁልፍ ወዳለፈው የ እርዳታ ገጽ ለ መመለስ
መቆጣጠሪያ የ ጽሁፍ ማምጫ ንግግር (CSV ፋይል ማምጫ)
ማስመሪያ
-
የ ግራ ወይንም የ ቀኝ ቀስት: አንድ ቦታ ወደ ግራ ወይንም ወደ ቀኝ ይሄዳል
-
Ctrl+የ ግራ ቀስት ወይንም Ctrl+የ ቀኝ ቀስት: ወዳለፈው ወይንም ወደሚቀጥለው መክፈያ ይዘላል
-
Ctrl+Shift+የ ግራ ቀስት ወይንም Ctrl+Shift+የ ቀኝ ቀስት: መክፈያውን አንድ ቦታ ወደ ግራ ወይንም ወደ ቀኝ ያንቀሳቅሳል
-
ቤት ወይንም መጨረሻ: ወደ መጀመሪያው ወይንም ወደ መጨረሻው ቦታ ይዘላል
-
Ctrl+ቤት ወይንም Ctrl+መጨረሻ: ወደ መጀመሪያው ወይንም ወደ መጨረሻው መክፈያ ይዘላል
-
Shift+Ctrl+ቤት ወይንም Shift+Ctrl+መጨረሻ: ወደ መጀመሪያው ወይንም ወደ መጨረሻው ቦታ መክፈያውን ያንቀሳቅሳል
-
የ ክፍተት ቁልፍ: ማስገቢያ ወይንም ማስወገጃ መክፈያ
-
ማስገቢያ ቁልፍ: መክፈያ ማስገቢያ (የ ነበረውን መክፈያ አይቀይርም)
-
ማጥፊያ ቁልፍ: መክፈያ ማጥፊያ
-
Shift+ማጥፊያ: ሁሉንም መክፈያዎች ማጥፊያ
-
ቀስት ወደ ላይ ወይንም ቀስት ወደ ታች: ሰንጠረዥ መሸብለያ አንድ ረድፍ ወደ ላይ ወይንም ወደ ታች
-
ገጽ ወደ ላይ ወይንም ገጽ ወደ ታች: ሰንጠረዥ መሽብለያ አንድ ገጽ ወደ ላይ ወይንም ወደ ታች
-
መዝለያ ቁልፍ (በ አይጥ በሚጎትቱ ጊዜ): መጎተቱን ይሰርዛል: መክፈያውን ወደ አሮጌው ቦታ ያንቀሳቅሳል
ቅድመ እይታ
-
የ ግራ ቀስት ወይንም የ ቀኝ ቀስት: ይምረጡ የ ግራ ወይንም የ ቀኝ አምድ እና ሌሎች ቦታዎችን ያጸዳል
-
Ctrl+የ ግራ ቀስት ወይንም Ctrl+የ ቀኝ ቀስት: ትኩረት ያንቀሳቅሳል ወደ ግራ ወይንም ወደ ቀኝ አምድ (ሌሎች ምርጫዎችን አይቀይርም)
-
Shift+የ ግራ ቀስት ወይንም Shift+የ ቀኝ ቀስት: የ ተመረጠውን መጠን ያሰፋል ወይንም ያጠባል
-
Ctrl+Shift+የ ግራ ቀስት ወይንም Ctrl+Shift+የ ግራ ቀስት: የ ተመረጠውን መጠን ያሰፋል ወይንም ያጠባል (ሌሎች ምርጫዎችን አይቀይርም)
-
ቤት ወይንም መጨረሻ ቁልፍ: ይመርጣል የ መጀመሪያውን ወይንም የ መጨረሻውን አምድ (ይጠቀሙ Shift ወይንም Ctrl እንደ መጠቆሚያ ቁልፎች )
-
Shift+የ ክፍተት ቁልፍ: መጨረሻ የ ተመረጠውን አምድ መጠን ይመርጣል ወደ አሁኑ አምድ ውስጥ
-
Shift+የ ክፍተት ቁልፍ: መጨረሻ የ ተመረጠውን አምድ መጠን ይመርጣል ወደ አሁኑ አምድ ውስጥ (ሌሎች ምርጫዎችን አይቀይርም)
-
Ctrl+A: ሁሉንም አምዶች ይመርጣል
-
Shift+F10: የ አገባብ ዝርዝር መክፈቻ
-
Ctrl+1 ... Ctrl+7: ማሰናጃ 1ኛ ... 7ኛ የ አምድ አይነቶች ለ ተመረጡት አምዶች
-
ቀስት ወደ ላይ ወይንም ቀስት ወደ ታች: ሰንጠረዥ መሸብለያ አንድ ረድፍ ወደ ላይ ወይንም ወደ ታች
-
ገጽ ወደ ላይ ወይንም ገጽ ወደ ታች: ሰንጠረዥ መሽብለያ አንድ ገጽ ወደ ላይ ወይንም ወደ ታች
-
Ctrl+ቤት ወይንም Ctrl+መጨረሻ: ሰንጠረዥ ወደ ላይ ወይንም ወደ ታች መሸብለያ
የ ተለዩ ባህሪዎች ንግግር - ማስገቢያ መቆጣጠሪያ
-
Tab በ ሁሉም መቆጣጠሪያ ንግግር ውስጥ ይቀያይራል
-
ምርጫ Alt+ቀስት ወደ ታች የ መቀላቀያ ሳጥን ይከፍታል: ማስገቢያ የ አሁኑን ማስገቢያ ከ መቀላቀያ ሳጥን ውስጥ ይመርጣል
-
የ ቀስት ቁልፎች በ ዋናው ምርጫ ቦታ ውስጥ ያንቀሳቅሳሉ: የ ክፍተት መደርደሪያ የ አሁኑን ባህሪ ይጨምራል ወደ ዝርዝር ባህሪዎች ውስጥ እንዲገቡ