መጎተቻ-እና-መጣያ ከ ዳታ ምንጭ መመልከቻ

ፈጣኑ መንገድ የ ዳታ ምንጭ ወይንም የ ሰንጠረዥ ሰነድ ኮፒ ለማድረግ: ወይንም ለ መፍጠር ፎርሞች የ ዳታ ምንጭ መሰረት ያደረገ: በ መጎተት-እና በ-መጣል ነው

በ አይጥ መጠቆሚያው ዳታ ኮፒ ማድረጊያ

ኮፒ ማድረጊያ በ መጎተቻ-እና-መጣያ

እርስዎ ከ ፈለጉ መጎተቻ-እና-መጣያ እንደ ነበር ለመመለስ: መጠቆሚያውን በ ሰነዱ ውስጥ ያድርጉ እና ይምረጡ ማረሚያ - መተው

የ ምክር ምልክት

እንዲሁም ኮፒ ማድረግ ይችላሉ በ መጎተት-እና-በመጣል ከ ሰነድ ውስጥ ወደ ዳታ ምንጭ:


የ ምክር ምልክት

የ ጽሁፍ ሰንጠረዥ ወይንም የ ተመረጠውን መጠን ሰንጠረዥ መጎተት ይቻላል በ መጠቀም መጎተቻ-እና-መጣያ ወደ ሰንጠረዥ ማጠራቀሚያ ከ ዳታ ምንጭ መቃኛ ውስጥ


የ ምክር ምልክት

መደበኛ ጽሁፍ ኮፒ ማድረግ ይቻላል በ መጠቀም መጎተቻ-እና-መጣያ ከ አንድ ሰነድ ውስጥ ወደ ዳታ ሜዳ ውስጥ ከ ዳታ ምንጭ መመልከቻ ውስጥ


ዳታ አጠቃቀም በ ጽሁፍ ሰነድ ውስጥ

እርስዎ የ ዳታቤዝ ሜዳ በ ጽሁፍ ሰነድ ውስጥ ማስገባት ይችላሉ: በ መጎተት የ ሜዳ ስም ከ አምድ ራስጌ ከ ዳታ ምንጭ መመልከቻ ወደ ሰነድ ውስጥ: ይህ በተለይ የሚጠቅመው የ ፎርም ደብዳቤዎች በሚያዘጋጁ ጊዜ ነው: በቀላሉ ይጎትቱ የሚፈልጉትን ሜዳዎች - የ ቤት አድራሻ ፎርም እና ሌሎችም - ወደ እርስዎ ሰነድ ውስጥ

ጠቅላላ መዝገብ ለማስገባት: ይምረጡ ተመሳሳይ ራስጌ እና ይጎትቱት ወደ ሰነድ ውስጥ: እርስዎ የ አይጥ ቁልፍ በሚለቁ ጊዜ: የ ዳታቤዝ አምዶች ማስገቢያ ንግግር ይታያል: እርስዎ ሁሉንም የ ዳታቤዝ ሜዳዎች ይጠቀሙ እንደሆን የሚወስኑበት: እና ዳታ ኮፒ ያደርጉ እንደሆን ወደ ሰነድ ውስጥ እንደ ጽሁፍ: ሰንጠረዥ ወይንም ሜዳዎች: ሁሉም የ ተመረጡት መዝገቦች ይገባሉ

ዳታ መፈጸሚያ ወደ ሰንጠረዥ ሰነድ ውስጥ

እርስዎ ማስገባት ይችላሉ አንድ ወይንም ተጨማሪ መዝገቦች ወደ አሁኑ ወረቀት ውስጥ ሰንጠረዥ በ መምረጥ ረድፎች ከ ዳታ ምንጭ መመልከቻ ውስጥ እና በ መጎተት እና በ መጣል ወደ ሰንጠረዥ ውስጥ: እርስዎ የ አይጥ ቁልፍ በሚለቁበት ቦታ ዳታ ይገባል

ወደ ጽሁፍ ፎርም መቆጣጠሪያዎች ማስገቢያ

እርስዎ ጽሁፍ በሚፈጥሩ ጊዜ ከ ዳታቤዝ ጋር የ ተገናኘ: እርስዎ ማመንጨት ይችላሉ መቆጣጠሪያዎች በ መጎተት-እና-በመጣል ከ ዳታ ምንጭ መመልከቻ ውስጥ

እርስዎ በሚጎትቱ ጊዜ የ ዳታቤዝ አምድ ወደ ጽሁፍ ሰነድ ውስጥ: እርስዎ ሜዳ ያስገቡ:እርስዎ ተጭነው ከያዙ የ Shift+ በሚጎትቱ ጊዜ የሚገባውን የ ጽሁፍ ሜዳ: ከ ተገቢው የምልክት ሜዳ ቡድን ጋር: እርስዎ ለ ፎርም የሚፈልጉትን የ ጽሁፍ ሜዳ ቀደም ብሎ ጠቅላላ የ ዳታቤዝ መረጃ የያዘ

መጎተቻ እና መጣያ በ LibreOffice ሰነድ ውስጥ

ስእሎች ኮፒ ማድረጊያ በ ሰነዶች መካከል

ኮፒ ማድረጊያ የ ሰንጠረዥ ቦታዎችን ወደ ጽሁፍ ሰነዶች

ንድፎችን ከ አዳራሽ ኮፒ ማድረጊያ

ንድፎች ወደ አዳራሽ መጨመሪያ

Please support us!