የ ሰንጠረዥ ንድፍ
ይህ ክፍል የያዘው መረጃ ስለ ዳታቤዝ ሰንጠረዥ እንዴት እንደሚፈጥሩ ነው በ ንድፍ መመልከቻ
መክፈቻ የ ዳታቤዝ ፋይል ከ ዳታቤዝ ውስጥ እርስዎ አዲስ ሰንጠረዥ በሚፈልጉበት: ይጫኑ በ ሰንጠረዥ ምልክት: ይምረጡ በ ሰንጠረዥ በ ንድፍ መመልከቻ መፍጠሪያ አዲስ ሰንጠረዥ ለ መፍጠር
በ ንድፍ መመልከቻ ውስጥ: እርስዎ አሁን ሜዳዎች መፍጠር ይችላሉ ለ እርስዎ ሰንጠረዥ
-
አዲስ ሜዳዎች ያስገቡ በ ረድፎች ውስጥ ከ ላይ እስከ ታች: ይጫኑ የ ሜዳ ስም ክፍል እና የ ሜዳ ስም ያስገቡ ለ እያንዳንዱ ዳታ ሜዳ
-
መጨመሪያ የ "ቀዳሚ ቁልፍ" ዳታ ሜዳ: ቤዝ ቀዳሚ ቁልፍ ይፈልጋል የ ሰንጠረዥ ይዞታዎችን ለ ማረም: ቀዳሚ ቁልፍ ልዩ ይዞታዎች አሉት ለ እያንዳንዱ ዳታ መዝገቦች: ለምሳሌ: የ ሂሳብ ሜዳ ያስገቡ በ ቀኝ-ይጫኑ የ መጀመሪያውን አምድ: እና ይምረጡ ቀዳሚ ቁልፍ ከ ዝርዝር ይዞታዎች ውስጥ: ያሰናዱ በራሱ ዋጋ ወደ "አዎ" ስለዚህ ቤዝ ራሱ በራሱ ለ እያንዳንዱ መዝገብ ዋጋ ይጨምራል
-
ከ ሚቀጥለው ክፍል በ ቀኝ በኩል: ይግለጹ የ ሜዳ አይነት እርስዎ ክፍሉን በሚጫኑ ጊዜ: እርስዎ መምረጥ ይችላሉ የ ሜዳ አይነት በ መቀላቀያ ሳጥን ውስጥ
እያንዳንዱ ሜዳ የሚቀበለው ዳታ ተመሳሳይ አይነት ብቻ ነው ከ ተወሰነው የ ሜዳ አይነት ውስጥ: ለምሳሌ: ጽሁፍ በ ቁጥር ሜዳ ውስጥ ማስገባት አይቻልም: ማስታወሻ ሜዳዎች በ የ ዳታቤዝ III አቀራረብ ውስጥ ማመሳከሪያ ናቸው ለ ውስጣዊ-አስተዳዳሪ የ ጽሁፍ ፋይሎች መያዝ የሚችሉ እስከ 64ኪቢ ጽሁፍ
እርስዎ ማስገባት ይችላሉ በ ምርጫ መግለጫ ለ እያንዳንዱ ሜዳ: የ ጽሁፉ መግለጫ ይታያል እንደ ጠቃሚ ምክር በ አምድ ራስጌዎች ላይ በ ሰንጠረዥ መመልከቻ ውስጥ
የ ሜዳ ባህሪዎች
ለ እያንዳዱ ለ ተመረጠው ዳታ ሜዳ ባህሪዎች ያስገቡ: እንደ ዳታቤዝ አይነት ይለያያል: አንዳንድ ማስገቢያ ክፍሎች ዝግጁ ላይሆኑ ይችላሉ
በ ነባር ዋጋ ሳጥን ውስጥ: ያስገቡ ነባር ይዞታዎችን ለሁሉም አዲስ መዝገቦች: እነዚህን ይዞታዎች በኋላ ማረም ይችላሉ
በ ማስገባት ያስፈልጋል ሳጥን ውስጥ: ሜዳው ባዶ እንደሚሆን ወይንም እንደማይሆን ይወስኑ
በ እርዝመት ሳጥን ውስጥ: የ ማጣመሪያ ሳጥን ዝግጁ ምርጫዎችን ይዞ ይታያል