የ ፊደል ቦታቦታ
ለ ባህሪዎች ቦታ: መጠን: ማዞሪያ እና ክፍተት ይወስኑ
ቦታ
ለ ባህሪ በትንንሽ ዝቅ ብሎ መጻፊያ ወይንም በትንንሽ ከፍ ብሎ መጻፊያ ምርጫ ማሰናጃ
በ ትንንሽ ከፍ ብሎ መጻፊያ
የተመረጠውን ጽሁፍ ፊደል መጠን ማሳነሻ እና ጽሁፉን ከ መሰረታዊ መስመር በላይ ከፍ ያደርገዋል
መደበኛ
በትንንሹ ከፍ ብሎ መጻፊያ ወይንም በትንንሹ ዝቅ ብሎ መጻፊያ አቀራረብ ማስወገጃ
በ ትንንሽ ዝቅ ብሎ መጻፊያ
የተመረጠውን ጽሁፍ ፊደል መጠን ማሳነሻ እና ጽሁፉን ከ መሰረታዊ መስመር በታች ዝቅ ያደርገዋል
ማሳደጊያ/ማሳነሻ በ
መጠን ያስገቡ እርስዎ መጨመር ወይንም መቀነስ የሚፈልጉትን የ ተመረጠው ጽሁፍ አንጻር ከ መሰረታዊ መስመር: መቶ ፐርሰንት ማለት ከ ፊደሉ እርዝመት እኩል ነው ማለት ነው
የ ፊደል መጠን ማነጻጸሪያ
የተመረጠውን ጽሁፍ ፊደል ማሳነስ የሚፈልጉበትን መጠን ያስገቡ
ራሱ በራሱ
ራሱ በራሱ መጠኑን ማሰናጃ የተመረጠውን ጽሁፍ ከፍ ማድረጊያ ወይንም ዝቅ ያደርገዋል ከ መሰረታዊ መስመር አንጻር
Rotation/scaling
ለ ተመረጠው ጽሁፍ የ ማዞሪያ እና መመጠኛ ምርጫ ማሰናጃ
0 ዲግሪዎች
የ ተመረጠውን ጽሁፍ አያዞርም
90 ዲግሪዎች
የ ተመረጠውን ጽሁፍ ማዞሪያ ወደ ግራ በ 90 ዲግሪዎች
270 ዲግሪዎች
የ ተመረጠውን ጽሁፍ ማዞሪያ ወደ ቀኝ በ 90 ዲግሪዎች
በ መስመሩ ልክ
የ ተመረጠውን ጽሁፍ ማስፊያ ወይንም ማመቂያ ከ ጽሁፉ በ ላይ ባለው መስመር ውስጥ ልክ እንዲሆን እና ከ ጽሁፉ በ ታች ባለው መስመር ውስጥ ልክ እንዲሆን
ስፋት መመጠኛ
ፐርሰንቴጅ ያስገቡ ለ ፊደል ስፋት የ ተመረጠው ጽሁፍ በ አግድም የሚሰፋበትን ወይም የሚያንስበትን
ክፍተት
በ እያንዳንዱ ባህሪዎች መካከል የሚኖረውን ክፍተት ይወስኑ
ክፍተት
የ ተመረጠው ጽሁፍ ባህሪ ክፍተት መካከል ምን ያህል መጠን እንደሚሆን ይወስኑ: ያስገቡ መጠኑን እንዲሰፋ ወይንም እንዲያንስ የሚፈልጉትን ጽሁፍ በ ማሽከርከሪያ ቁልፍ ውስጥ
ክፍተት ለ መጨመር አዎንታዊ ዋጋ ያሰገቡ: ክፍተት ለ መቀነስ አሉታዊ ዋጋ ያስገቡ
ጥንድ ክፍተት
ራሱ በራሱ የ ባህሪ ክፍተት ማስተካከያ ለ ተወሰነ ፊደል መቀላቀያ
Kerning ዝግጁ የሚሆነው ለ አንዳንድ የ ፊደል አይነቶች ነው: እና የ እርስዎን የ ማተሚያ ድጋፍ ምርጫ ይፈልጋል